ከሰማይ የወረዱ /ሰማያውያን/ መፅሃፍት

ከሰማይ የወረዱ /ሰማያውያን/ መፅሃፍት 

  •  በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት
  • የተከበረው ቁርኣን.. የመጨረሻው መፅሃፍ
  • የተውራት /ኦሪት/ መበረዝ
  • የኢንጂል /ወንጌል/ መበረዝ
  • የተከበረው ቁርኣን የቀደሙትን መፅሃፎች እውነትነት ስለማረጋገጡ
  • ወደ እውነት የሚያደርሰው መንገድ
 ከሰማይ በወረዱት መፅሃፍት ማመን (አል-ኢማን ቢኩቱብ አስ-ሰማዊያ) ከስድስቱ የእምነት ምሶሶዎችን (አርካን አል-ኢማን) ውስጥ በሶስተኛ ደለጃ የተጠቀሰ ነው። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አበይት የእምነት ክፍል በዝርዝል እንመለከታለን።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ወደ መልእክተኞቹና ነቢያቶቹ ወህይ ያደረጋቸው /በራእይ የገለፀላቸው/ የሆኑ ምክሮችና ትምህርቶች አሉ። ከነኚህም መካከል በመፅሀፍ መልክ የተጠረዙ ያሉ ሲሆን ከነኚህም ውጭ እኛ የማናውቃቸው የሆኑ አሉ። ሁሉም ነቢይ የተላከበትን መልእክት ወደ ህዝቦቹ አድርሷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ [٢:٢١٣]
“ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)። አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ። ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ።” (አል-በቀራህ 2፤ 213)
فَإِنْ كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ جَاءُوا بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَالْكِتَابِ الْمُنِيرِ [٣:١٨٤]
“ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በጽሑፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 184)
በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት 
1. በነቢዩ ሙሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ተውራት /ኦሪት/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

إِنَّا أَنْزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدىً وَنُورٌ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِنْ كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ [٥:٤٤]

“እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን። እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ። ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 44)

وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنْزَلَ اللَّهُ عَلَى بَشَرٍ مِنْ شَيْءٍ قُلْ مَنْ أَنْزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَى نُوراً وَهُدىً لِلنَّاسِ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيراً [٦:٩١]
“ ‘አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም’ ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም። (እንዲህ) በላቸው፡- ‘ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው?’ ” (አል-አንዓም 6፤91)
2. በነቢዩ ዒሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ኢንጂል /ወንጌል/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَقَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ [٥:٤٦]

“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን። ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 46)
3. በነቢዩ ዳውድ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ዘቡር
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَآتَيْنَا دَاوُدَ زَبُوراً [١٧:٥٥]
“ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል።” (አል-ኢስራእ 17፤ 55)

4. በነቢዩ ኢብራሂም እና በነቢዩ ሙሣ (ዓ.ሠ) ላይ የወረዱት ፅሁፎች /ሱሁፍ/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ﴿٣٦﴾ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ﴿٣٧﴾ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ﴿٣٨﴾ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ﴿٣٩﴾ وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ﴿٤٠﴾ ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ﴿٤١﴾ وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنتَهَىٰ ﴿٤٢﴾

“ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል። መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው።” (አን-ነጅም 53፤36-42)
قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ﴿١٤﴾ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ ﴿١٥﴾ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ﴿١٦﴾ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ﴿١٧﴾ إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ﴿١٨﴾ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ ﴿١٩﴾

“የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ። የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ። ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ። መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን። ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው። በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ።” (አል-አዕላ 87፤ 14-19)

ከአቢ ዘር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው ለአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

“በኢብራሂም ላይ የወረዱ ፅሁፎች ምን ይመስሉ ነበር? በማለት ጠየቅኳቸው። እርሣቸውም ‘ሁሉም ምሣሌዎች ናቸው።’ በማለት መለሱ።

أيها الملك المسلط، المبتلى، المغرور، إنى لم أبعثك بتجمع الدنيا بعضها على بعض، ولكنى بعثتك لترد عنى دعوة المظلوم، فإنى لا أردها وإن كانت من كافر

‘አንተ አምባገነን፣ የተፈተንክና የተታለልክ ንጉስ ሆይ! እኔ ዱኒያን አንዷን ባንደኛዋ ላይ እንድትሰበስብ አይደለም የላክሁህ። ነገር ግን የላክሁህ የተበዳይ ስሞታን ከኔ ምላሽ እንድትሰጥ ነው። እኔ እሷ /የተበዳይ ስሞታ/ የከሀዲ እንኳን ብትሆን ምላሽ ሣልሠጥ የምተው አይደለሁም።’

وعلى العاقل – ما لم يكن مغلوبًا على عقله – أن يكون ساعات:
فساعة يناجى فيها ربه.
وساعة يحاسب فيها نفسه.
وساعة يتفكر فيها فى صنع الله عز وجل.
وساعة يخلو فيها لحاجته من المطعم والمشرب

‘ማንኛውም ብልህ የሆነ ሰው በአእምሮው ጤነኛ እስከሆነ ድረስ የተከፋፈሉ ሰዓታት ሊኖሩት ይገባል:-
ከጌታው የሚመሣጠርበት ሰዓት
እራሱን የሚገመግምበት ሰዓት
የአላህ ሥራዎችን በመመልከት ጊዜ ሰጥቶ የሚያስተነትንበት ሰዓት
ምግብና መጠጥን ለመሣሰሉ ጉዳዮች እራሱን የሚያገልበት ጊዜ።’

وعلى العاقل، ألا يكون ظاعنًا إلا لثلاث:
تزود لمعاد، أو لمعاش.
أو لذة فى غير محرم.

‘ብልህ ሰው ለሦስት ነገሮች ካልሆነ ትልቅ ትኩረት መስጠት የለበትም፡-
ለመመለሻው /ለአኺራው/ አለያም ለኑሮው /ለምድር ላይ ህይወቱ/ ለመሠነቅ
ሀራም ባልሆነ ነገር እራሱን ለማስደሠት።’

وعلى العاقل أن يكون بصيرًا بزمانه، مقبلاً على شأنه، حافظًا للسانه؛ ومن حسب كلامه من عمله قل كلامه إلا فيما يعنيه

‘ብልህ ሰው ስላለበት ዘመን ሁኔታ በጥልቀት ማወቅ አለበት። የራሱንም ሁኔታ መገምገም ይኖርበታል። ከንግግሩና ከሥራው አንፃር ምላሱን ጠባቂና በሚያገባው ነገር ላይም ብቻ የሚናገር መሆን ይገባዋል።’
‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የሙሣ ፅሁፎችስ ምን የያዙ ነበሩ?’ እርሣቸውም ‘ሁሉም በጥበባዊ ምክሮች የተሞሉ ናቸው’ አሉ።

عجبت لمن أيقن بالموت، ثم هو يفرح.
‘ሞት እንዳለበት እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የሚደሰት ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن بالنار، ثم هو يضحك.

‘እሣት እውነት መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የሚስቅ ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن بالقدَر، ثم هو ينصب

‘ቀደር እውነት መሆኑን እያወቀ የሚደክመው ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن رأى الدنيا وتقلبها بأهلها، ثم اطمأن إليها.

‘ዱኒያንና በሰዎች የመቀየር ባህሪዋን እያስተዋለ በሷ የሚረጋ ሰው ይገርመኛል።’

عجبت لمن أيقن الحساب غدًا، ثم لا يعمل.

‘ነገ ምርመራ ያለ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሣለ የማይሠራ ሰው ይገርመኛል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይምከሩኝ።’ አልኳቸው። እርሣቸውም፡-

أوصيتك بتقوى الله، فإنها رأسُ الأمر كله

‘አላህን በመፍራት ይሁንብህ አደራህን። እሱ የነገሮች ሁሉ ቁንጮ ነውና።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ይጨምሩኝ’ አልኳቸው።

عليك بتلاوة القرآن، وذكر الله ، فإنه نور لك فى الأرض، وذخر لك فى السماء

‘ቁርኣንን በማንበብና አላህን በማውሣት ይሁንብህ አደራህን። እሱ በምድር ላይ ብርሃን በሰማይ ቤትም ሀብት ይሆንሃል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ’ አልኳቸው።

إياك وكثرة الضحك، فإنه يميت القلب، ويذهب بنور الوجه

‘ሣቅ አታብዛ እሱ ቀልብን ይገድላል፣ የፊትን ብርሃን ይወስዳል።’

‘ይጨምሩኝ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!’።

عليك بالجهاد، فإنه رهبانية أمتى

‘በጅሃድ ላይ በርታ አደራህን፤ እሱ የህዝቦቼ ምንኩስና ነው።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’ አልኳቸው።

أحبَّ المساكين وجالسهم

‘ድሆችን ውደድ ከነሱም ጋር ተቀማመጥ።’ አሉኝ

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

انظر إلى من هو تحتك، ولا تنظر إلى ما هو فوقك، فإنه أجدر أن لا تزدرى نعمة الله عنك

‘ከበታችህ ወዳለው ሰው ተመልከት። ከበላይህ ወዳለው አትመልከት። ይህም አላህ ባንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ይበልጥ እንድታስታውስ ያግዝሃልና።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

قل الحق وإن كان مُرًا

‘የቱን ያህል መራር ቢሆንም እንኳ እውነትን ከመናገር ወደኋላ አትበል።’

‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሁንም ይጨምሩኝ።’

ليردك عن الناس ما تعلمه من نفسك، ولا تجد عليهم فيما تـ أتى، وكفى بك عيبًا أن تعرف من الناس ما تجهله من نفسك، وتجد عليهم فيما تـ أتى

‘አንተ የማትሰራበት ስትሆን ስለራስህ የምታውቀው ነገር ስለሰው ከማውራት ይቆጥብህ። አንተ የምትሠራበት ስትሆን በራስህ ላይ ያላስተዋልከው ነገር በሰው ላይ ማየትህ ከነውር ይብቃህ።’ አሉኝ።

ከዚያም በእጃቸው ደረታቸውን መታ በማድረግ፡-

يا أبا ذر، لا عقل كالتدبير، ولا ورع كالكف، ولا حسب كحُسن الخُلُق

‘አባዘር ሆይ! እንደ ማስተንተን አዕምሮ የለም፤ እንደ መታቀብ ፍራቻ የለም፤ እንደ መልካም ሥነ-ምግባር ክብር የለም።’ አሉ።” (ኢብኑ ሂባንና ሀኪም ዘግበውታል)

5. የተከበረው ቁርኣን የመጨረሻው ሰማያዊ መፅሃፍ ነው።

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ﴿٢﴾ نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ ﴿٣﴾ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَانَ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَاللَّهُ عَزِيزٌ ذُو انتِقَامٍ ﴿٤﴾

“አላህ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። (እርሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው። ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ። ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል። (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)። ፉርቃንንም አወረደ።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 2-4)
የቁርኣን መለያዎች
የተከበረው ቁርኣን ከሌሎች ከቀደሙት ሰማያውያን መፅሃፎች የሚለይበት ባህሪ አለው። ከነሱም መካከል
1. በተውራትና በኢንጂል የወረዱ አምላካዊ አስተምህሮዎችን፣ ሌሎችንም አላህ (ሱ.ወ) ያወረዳቸውን ምክሮችን በሙሉ ጠቅሎና ጨምቆ የያዘ መሆኑ ነው። ቁርኣን አላህን ብቻ ማምለክ፣ በመልእክተኞቹ ማመን፣ የምንዳውን ቀን እውነትነት መቀበል፣ እውነትን ቀጥ አድርጎ ማቆም ግዴታ ስለመሆኑ፣ በመልካም ስነ-ምግባር መታነፅንና የመሣሠሉትን በቀደምት መፅሀፍት ውስጥ የተጠቀሱትን እውነታዎች ሁሉ አጋዥና አጠናካሪ ሆኖ ነው የመጣው።
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقاً لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِناً عَلَيْهِ فَاحْكُمْ بَيْنَهُمْ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ وَلا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ عَمَّا جَاءَكَ مِنَ الْحَقِّ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنْكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجاً [٥:٤٨]
“ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን። በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል። ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን።” (አል ማኢዳህ 5፤ 48)
ይህም ማለት አላህ (ሱ.ወ) የተከበረውን ቁርኣን ከእውነት ጋር አቆራኝቶ፣ በቀደሙ ነቢያት ላይ የወረዱ አምላካዊ መፃህፍትን አረጋጋጭና ተቆጣጣሪ አድርጎ ነው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ያወረደው ማለት ነው። በቀደሙት መፃህፍት ውስጥ የመጡትን እውነቶች ያፀድቃል፣ በውስጣቸው የገቡትን ውሸትና የመበረዝ ሂደቶች ይገልፃል። ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) የሱን ነቢይ በሰዎች፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብና በመፅሃፉ ባልተቤቶች መካከል ከስሜት በራቀ መልኩ አላህ በቁርኣኑ ውስጥ ባወረደው ነገር ፍርድ እንዲሠጥ ያዘዋል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
شَرَعَ لَكُمْ مِنَ الدِّينِ مَا وَصَّى بِهِ نُوحاً وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَى وَعِيسَى أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ [٤٢:١٣]
“ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ። ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)።” (አሽ-ሹራ 42፤ 13)
ቁርኣን በመምጣቱ ምክኒያት ከዚህ በፊት ይሠራባቸው የነበሩ የቀደምት ነቢያት ህግጋቶች በኢስላማዊው ህግ ተሽረዋል። የእስልምና ህግጋትም የመጨረሻው ህግና ለሁሉም ዘመንና ቦታ ምቹና ዘላለማዊ እንዲሆን ተደርጎ ተደንግጓል። በዚህም እምነት ሁሉ አንድ ሆነ፤ ህግጋትም ለሰው ልጆች ሁሉ አንድ እንዲሆኑ ተደረገ።
2. የቁርኣን አስተምህሮ የሰውን ልጅ ወደ ቀናው መንገድ ለመምራት የመጣ የመጨረሻው የአላህ ንግግር ነው። አላህ (ሱ.ወ) ለዘላለሙ እንዲቀር፣ ለዘመናትም እንዲኖር መርጦታል። ሌሎችን ሰማያውያን መፅህፍት የቀየሩ፣ የለወጡና፣ የበረዙ እጆች እንዳይገቡበት ጠብቆታል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ ﴿٤١﴾ لَّا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنزِيلٌ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ ﴿٤٢﴾
“እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)። ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም። ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደው።” (ፉሲለት 41፤ 41-42)
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ [١٥:٩]
“እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው። እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን።” (አል-ሂጅር 15፤ 9)
የዚህ ሁሉ ዋናው ዓላማ የአላህ ማስረጃ በሰዎች ላይ ሁሉ ይፋ ይሆን ዘንድ ነው። አላህ መሬትንና እላዩዋ ያሉትን ሁሉ እስኪወርስ ድረስ።
3. አላህ (ሱ.ወ) ዘላለማዊነትን የፈለገለት ይህ ቁርኣን አንድ ቀን ከሳይንሳዊ እውቀት ጋር ይጋጫል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው። ፍጥረተ ዓለሙም የሱ ሥሪት ነው። ሥራውና ንግግሩ ፈፅሞ ሊጋጩ አይችሉም። ባይሆን አንደኛው ሌላኛውን ያጠናክራል። በመሆኑም የዛሬዎቹ ሣይንሣዊ ምርምሮች የቁርአንን አስተምህሮ የሚያረጋግጡ ሆነው መጥተዋል። እነኚህም ቀጥሎ ያለውን የተከበረውን የአላህን (ሱ.ወ) ንግግር ለማፅደቅ ነው።
سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الآفَاقِ وَفِي أَنْفُسِهِمْ حَتَّى يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ [٤١:٥٣]  
“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን። ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?” (ፉሲለት 41፤ 53)
4. አላህ (ሱ.ወ) ቃሉ እንዲሠራጭ፣ ወደ ሰዎች ሁሉ ልቦናና ጆሮ እንዲደርስና ወደ ተጨባጭ ህይወትም እንዲለወጥ ይፈልጋል። ይህም ሊሆን የሚችለው በቃል ለመሸምደድ ለመገንዘብና ለማስታወስ የገራ እንደሆነ ነው። ለዚህም ነው ቁርኣን ገር ሆኖ የመጣው። ለመረዳት አሊያም ለመሥራት በሰው ላይ የሚከብድ ነገር የለውም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِنْ مُدَّكِرٍ [٥٤:١٧]  
“ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው። ተገንዛቢም አልለን?” (አል-ቀመር 54፤ 17)
ገርነቱን ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል ወንዶችና ሴቶች፣ ትንሹም ይሁን ትልቁ፣ ድሃውና ሀብታሙ እሱን በቃል ለማጥናት መቻላቸውና በቤቶቻቸውና በመስጅዶቻቸውም ውስጥ ዘወትር ማንበባቸው ነው። ዛሬ ዛሬ ከየትኛውም ንባብ በላይ የቁርኣን አንባቢዎች ድምፅ በየቦታው ይሠማል። ከቁርኣን በስተቀር የትኛውም መፅሃፍ የዚህ ዓይነት ደረጃ አግኝቶ አላየንም። ይህ በርግጥም አላህ (ሱ.ወ) ለቁርኣን የሰጠው መለያ ነው።
በተፅእኖውና በምርጥ ምልከታዎቹ፤ በሚያነሣቸው ጉዳዮችም ሆነ በሌላ ዛሬም ድረስ ቁርኣንን የሚያህል አልተገኘም። ይህም ቁርኣንን ከመፅሃፎች ሁሉ እጅግ በላጭና ተመራጭ ያደርገዋል።
የተውራት መበረዝ
በሙሣ (ዐ.ሠ) ላይ በወረደው ተውራት ማመን ከሙስሊም የእምነት መሠረቶች ውስጥ አንዱ ነው። በሱ ውስጥ ብርሃንና የቅን መንገድ ምልከታ መኖሩን አወድሦ አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ ውስጥ ነግሮናል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْراً لِلْمُتَّقِينَ [٢١:٤٨]
“ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው።” (አል-አንቢያእ 21፤ 48)
ነገር ግን በሙሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ተውራት ዋናው ቅጂው ዛሬ የለም። ዛሬ ያለው የተውራት መፅሃፍ በብዙ ሰው እጅ የተፃፈ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ መበረዝና መከለስ ገብቶበታል። ኡስታዝ ሙሀመድ ፈሪድ ወጅዲ በዚሁ ዙሪያ ሲናገሩ “ተጨባጭ ከሆኑት መበረዙን ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል በክርስቲያኖች ዘንድ የሚገኘውና በአይሁዶች ዘንድ የሚገኘው ኦሪት መለያየቱ ነው።” ብለዋል
ቁርኣንም ይህ የአይሁዶች መፅሀፍ ለውጥ እንደገባበት አረጋግጧል። ለውጥ በማድረግ፣ በመጨመር በመቀነስ፣ አምላከዊ ያልሆኑ አስተምህሮዎችን ያስገቡበትን አይሁዶችንም ወቅሷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
أَفَتَطْمَعُونَ أَنْ يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِنْ بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُونَ [٢:٧٥]
“(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?” (አል በቀራህ 2፤75)
አይሁዶች የአላህን ኪታብ ተዳፍረዋል። የያዘውን እውነት ለመደበቅ ሲሉም ቀያይረውታል። በኦሪት ውስጥ የአላህን ማስጠንቀቂያ ብዙም ግምት አልሠጡትም። ከትክክለኛው ተውራት እነሱ ዘንድ ያለው ከፊሉ ብቻ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
مِنَ الَّذِينَ هَادُوا يُحَرِّفُونَ الْكَلِمَ عَنْ مَوَاضِعِهِ [٤:٤٦]
“ከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ።” (አን-ኒሣእ 4፤ 46)
አሁን ያለው ተውራት በቁርኣን የመተቸቱ ትክክለኛነት ሁሉም ይዘቱ ያ አላህ (ሱ.ወ) የብርሃንና የቅናቻ ምንጭ አድርጎ ለሙሣ የሠጠው ባለመሆኑ ነው። በተውራት ውሰጥ ስለ አላህ ባህሪ ለሱ በማይገባ መልኩ የተቀመጠ ሲሆን በርካታ ለአላህ መፅሃፍ የማይገቡ ፅሁፎችም ተካተውበታል።
ሌላው ደግሞ በሱ ውስጥ የነቢያትን ክብር በሚነካ መልኩ የመጣውና ከጥብቅናቸውና ከመልካም ሥነምግባራቸው፣ እንዲሁም ካላቸው የከበረ ደረጃ ጋር የሚጋጨው አስተምህሮው ነው። ለምሣሌ- ነቢዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሠ) “ውሸታም” ብለዋቸዋል። ነቢዩ ሉጥ (ዐ.ሠ) ደግሞ በእህታቸው ላይ ዝሙት እንደፈፀሙ ያስወሩባቸዋል። ነቢዩ ሃሩንን (ዐ.ሠ) ደግሞ ኢስራኢሎችን ጥጃን ወደ ማምለክ ጠርተዋቸዋል ይላሉ። ነቢዩ ዳውድን (ዐ.ሠ) በኦሪያ ሚስት ዝሙት እንደፈፅሙ አድርገው ስማቸውን ሲያጠፉ ነቢዩ ሱለይማንን (ዐ.ሠ) ደግሞ በሚስታቸው ለመወደድ ሲሉ ጣኦትን እንዳመለኩ ያነውሯቸዋል።
ከዚህ በላይ ለመበረዙ ማስረጃ አያስፈልግም። ከአይሁድ ሰዎች ውስጥ መልካሞቹ የሚባሉት እንኳ በዚህ ነገር አምነው ተቀብለዋል። “አይሁዳዊነት” በሚለው መፅሃፋቸው ውስጥ ሃካም ባሬዝ አጆሊያ ዌል ይህንኑ ፅፎታል።
የወንጌል መበረዝ
በዒሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ኢንጂል /ወንጌል/ እንደ ተውራት ሁሉ የአላህ ቃል ናቸው። በነሱም ውስጥ የቅኑ መንገድ ምልከታና ብርሃን አለ። ሆኖም ግን ኦሪትን ያገኘው የመበረዝ ሂደት ወንጌልንም አግኝቶታል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ ﴿١٤﴾ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ ﴿١٥﴾
“ከእነዚያም እኛ ክርስቲያኖች ነን ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን። በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት። ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው። አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል። የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ። ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 14-15)
ለዚህ ማስረጃ በክርስቲያኖች እጅ የሚገኙ የወንጌል መፅሃፍትን ማየቱ በቂ ነው። ዛሬ ያሉት አራቶቹ ከሰባ በላይ ከሚሆኑ ወንጌሎች መካከል የተመረጡ ናቸው። እነኚህ አራቶቹ ቢሆኑም በዋናነት የነቢዩ ዒሣን (ዐ.ሠ) ታሪክ የያዙ ሲሆን ደራሲዎቻቸውም ይታወቃሉ። ሥማቸውም በነሱ ላይ ተፅፏል። ክርስቲያን ሀያሲ ምሁሮች እንደሚሉት የወንጌል አስተምህሮዎች የሀዋሪያቶችና ወደ ዒሳ እጅግ የሚቀርቡ ሰዎች አስተምህሮዎች ሣይሆኑ የጳውሎስ ሀሳቦች ናቸው።
በአንድ ወቅት በፓሪስ ከንጉሣውያን ቤተሰቦች ከሆኑት ከአንዱ ቤት የባርናባስ ወንጌል / Gospel of Barnabas/ የተገኘ ሲሆን ይህም መፅሃፍ ከአራቱ ወንጌሎች በእጅጉ ይለያል።
ቁርዓን “የቀደሙትን መፅሃፎች እውነተኝነት ያረጋጋግጣል” ስንል ምን ማለታችን ነው?
ተውራትና ኢንጂል በርግጠኝነት መበረዝና መከለስ ተካሂዶባቸው ከሆነና ይህም መሆኑ በአንድ በኩል በቁርኣን አንቀፆች በሌላ በኩል ደግሞ በተጨባጭ በሚታየው ነገር ከተደረሠበት፤ ቁርኣን የመጣው “የቀደሙ ኪታቦችን እውነትነት ለማረጋገጥ ነው” ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
የዚህ ትርጉሙ- ቁርኣን በርግጥም በነሱ ውስጥ የወረደውን እውነታ ለማጠናከር የመጣ ነው። ይህም ሲባል ከላይ እንደተገለፀውም አላህን በብቸኝነቱ ማምለክን፣ መልእክቱን እውነት ብሎ መቀበልን፣ የምንዳ ቀን መኖሩን ማመንን፣ እውነትንና ፍትህን ማስፈንን፣ በመልካም ስነምግባር መታነፅንና የመሣሠሉትነ የሚያጠቃልል ሲሆን በተመሣሣይ ሁኔታም በነሱ ላይ ተቆጣጣሪ፤ በመቀየር፣ በመጨመርና በመቀነስ፣ በመበረዝና በሌላም መልኩ የተደረጉባቸውን ለውጦችና በውስጡ የተፈጠሩትን ስህተቶች ገላጭ ነው።
የእምነቱ ሰዎች በአላህ ሥም ሰዎችን በማታለል በሰማያውያን መፅሃፎች ውስጥ ያስገቡት ስህተቶች የወጡና የጠፉ እንደሆነ ያኔ እውነታው ግልፅ ወጣ። ቁርኣን፣ ተውራትና ኢንጂልም ተጣጣሙ ማለት ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَسْتُمْ عَلَى شَيْءٍ حَتَّى تُقِيمُوا التَّوْرَاةَ وَالأِنْجِيلَ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْكُمْ مِنْ رَبِّكُمْ [٥:٦٨]
“እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደእናንተ የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም በላቸው።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 68)
ከውሸትና ጥመት ከፀዱ በኋላ እንጂ እነሱን ማቆም አይቻልም።
ወደ እውነታ የሚያደርሰው መንገድ
እውነትን የሚፈልግና ወደ ትክክለኛው አምላካዊ አስተምህሮ መድረስ የሚከጅል ሰው ከተከበረው ቁርኣን ውጭ አማራጭ ሊኖረው አይገባም። እሱ መሠረቱ የተጠበቀ መፅሃፍ ነው። አስተምህሮውም ከመበረዝና ከመከለስ የፀዳ ነው። ህዝቦች ከሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እና ከአላህ (ሱ.ወ) በቀጥታና በተዋረድ አግኝተውታል። የሱ ዓይነት መፅሃፍ ፈፅሞ የለም። እሱ የላቀና የመጠቀ መርህ ነው። የመንገዶች ሁሉ ጠንካራ፣ የሥርኣቶች ሁሉ በላጭ፤ ከእምነት ከአመለካከት፣ ከአምልኮ፣ ከሥርኣት፣ ከግንኙቶች.. የሰው ልጆች የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ነው። ቁርኣን የያንዳንዱን ሰው ሥነምግባር ምሉእ ለማድረግ፣ ለጥሩ ቤተሰብ፣ ለበጎ ማህበረሰብ፣ ለፍትሃዊ መንግስት፤ ሀቅን ለሚያቆም፣ በደልን ለሚያነሣና ጠላትነትን ለሚያስወግድ ጠንካራ ሥርኣት ትልቅ ዋስትና ነው። በምድር ላይ አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች የሰጠውን የተተኪነት ሀላፊነት (አል-ኺላፋ) ሚና ለማረጋገጥም ብቸኛው መንገድ እሱ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ ﴿١٥﴾ يَهْدِي بِهِ اللَّهُ مَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَهُ سُبُلَ السَّلَامِ وَيُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِهِ وَيَهْدِيهِمْ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ ﴿١٦﴾
“የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ። ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ። አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል።” (አል-ማኢዳህ 6፤ 15-16)