የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአመራር ብቃት

የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአመራር ብቃት

ነቢያዊ አመራር ስንል ዘመናዊ የአመራር ንድፈ ሀሳብና ስልትን ከነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ ) አርዐያነት አንጻር መመልከት መቻል ነው:: ነቢዩ በሁሉም የህይወት መስኮች ምሳሌ በመሆናቸው ምጡቅ የሆነውን የአመራር ስልታቸውን በአንክሮ መመልከት ያስፈልጋል:: ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ሃገር መሪ፤ እንደ ቤተሰብ አስተዳዳሪ፤ እንደ ጦር መሪ፤ እንደ መምህር፤ እንደ ሃይማኖት ሰባኪ፤ እንደ ሃይማኖት አባት፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ የህይወታችን ዘርፍ ምርጡ አርአያችን ናቸው፡፡እንደ ሙስሊም ከ23_ አመት የነቢይነት ታሪክ የሚቻለንን ያህል የአመራር ልምድና ስልቶች አነጥረን ማውጣትና መጠቀም ይኖርብናል:: በዚህ አጭር ፅሁፍ ተወዳጁ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) በአመራር ዘርፍ የነበሯቸውን ብቃት ከዘመናዊ አመራር መርሆች አንጻር ለማየት እንሞክራለን፡፡
ብዙ ግዜ ሙስሊሞች የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) አመራር ከዳዓዋና ከአገር መሪነት ያለውን ብቻ በመመልከት ሌሎች ሚናዎቻቸውን ቸል ስንል ይስተዋላል:: የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአመራር ሚና ሲነሳ ብዙውን ጊዜ ከጦር አውድማ ጋር ይያያዛል 1 ነገር ግን ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከጦር አመራርነት ውጪ ሌሎች በርካታ የአመራር ሚናዎችን ተጫውተዋል፡፡ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያሳለፏቸውን ጦርነቶች በጊዜ ድምር ብንመለከተው ምናልባት ከህይወታቸው ከሁለትና ሶስት ወራት ያልበለጠ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) በ 40 አመታቸው ነብይነት ተሰጥተዋል:: ከዛ በፊት ለዚሁ አመራር ብቃት ሊያዘጋጇቸው ሂደቶች አልፈዋል:: እረኛ ሆነው አገልግለዋል፤ ነጋዴና የንግድ ቅፍለት መሪ ሆነው ሰርተዋል፡፡ በጎሳቸው ውስጥም ወደ ጎሳ መሪነት የሚያደርሳቸው አቅጣጫ ይዘው ነበር ከኸድጃ ጋር በመሰረቱት ትዳርም የቤተሰብ አስተዳዳሪነት ሚና መጫወታቸውን የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) በአርባ አመታቸው ለመልእክተኝነት መመርጣቸው ለቀጣይ 23 አመታት በርካታ የአመራር ሚናዎች ተጫውተዋል፡፡

1.ነብያዊ አመራር ስነ-ምግባር     (Ethics)

ስነ-ምግባር በዘመናዊ የፖለቲካና ድርጅታዊ አመራር ዘርፍ አስፈላጊነቱ በጣም እየጎላ ሆኖም እየጠፋ ያለ ባህሪይ ነው፡፡የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስነ-ምግባር መገለጫዎች ከእምነታቸውና ከመለኮታዊው መመሪያ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ነው፡፡እንደ እውነተኝነትና ታማኝነት ያሉ መልካም ስነ-ምግባራት ለማንኛውም የአመራር ዘርፍ መሰረታዊ ግብአቶች ናቸው፡፡እውነተኝነትና ታማኝነት በማንኛውም ዘርፍ የተሰማራ መሪ የግድ ሊኖሩት የሚገቡና የአመራር ሂደቱ ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የመልካም ስነ-ምግባር መገለጫዎች ናቸው፡፡ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመልካም ስነምግባርና በታላቅ እሴቶች የቆሙ እንደነበሩ ከነብይነት በፊት “ታማኙ” እና “እውነተኛው” በሚል ቅፅል ስም መጠራታቸው ግልፅ ምስክር ነው፡፡ ለዚህም ነው የመካ ሰዎች በጠላትነት ከፈረጇቸው በኌላም ቢሆን ንብረቶቻቸውን በአደራ ከሚያስቀምጡባቸው ጥቂት ታማኝ ሰዎች አንዱ ለመሆን የቻሉት፡፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጥግ የደረሰ ታማኝነት መካውያንን ለሳቸው ከነበራቸው ጥላቻ ጋር ባላደራነታቸውን በተግባር እንዲመሰክሩ አስገድዷቸዋል፡፡
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መልካም ስነ-ምግባር በማህበረሰባዊ ጉዳዮች በዘለለ በቤተሰባዊ ጉዳዮች ላይም ጭምር በሰፊው ይንፀባረቅ ነበር ፡፡ በአንድ ወቅት እናታችን አኢሻ(ረ.ዐ) ስለ አንዲት ሴት አካላዊ ገፅታ ለመግለፅ በሞከረችበት ጊዜ የተፈጠረው ክስተት ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ሌሎች በጎ ያልሆኑ ነገሮች በምልክትም ቢሆን ማንጸባረቅ ካሉን የስነ-መምግባር እሴቶችና ግብረገባዊ መርሆች ጋር ስለማይሄድ ይህን ማድረግ የለብንም ሲሉ አስታውሰዋታል፡፡ የአኢሻ (ረ.ዐ) ንግግር ስንመለከተው ያን ያህል የተጋነነ ባይሆንም ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የሰጡት ምላሽ ግን ለስነ-ምግባር እሴቶቻቸው ያላቸውን ጥልቅ ስሜት ያሳየ ነበር፡፡

2.ነብያዊ የአመራር ብቃት ታዛዥነት / ታማኝነት /(Loyalty)

ተከታዮችን ማፍራት መቻል ከአመራር ፅንሰ-ሀሳቦች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በሰዎች ልብ ውስጥ ራዓይህን መትከልና ለራእዩ መሳካት ሰዎች ነቅተው እንዲሰሩ ማስቻል የመሪዎች ሚና ነው፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ በሰዎች ዘንድ የጠበቀ ታማኝነት ሊኖረው ይገባል፡፡ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከጅብሪል መጀመሪያ ዋህይ ሲወርድላቸው ባለቤታቸው ከድጃ(ረ.ዐ) እነ አቡበከር (ረ.ዐ) ያለምንም ማንገራገር አምነው እንዲቀበሉ ብሎም አጋር እንደሆኗቸው ያደረጋቸው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከዚያ ክስተት በፊት የገነቡት የጠለቀ ታማኝነት መሆኑን እንረዳለን፡፡
በስራ ቦታ ፤በቤተሰብ ፤በማህበራዊ እንቅስቃሴዎችና በሌሎች ዘርፎች በሰዎች ዘንድ ታማኝነትን ማግኘት ከባዱ ስራ ነው፡፡ለአላማችን ታማኝ የሆኑ ሰዎቸችን ለማፍራት በቅድሚያ ራሳችን ለአላማችን ታማኝ ሆነን መገኘት ይኖርብናል፡፡ለሰዎች ታማኝ ስንሆን ሰዎች ለኛ ታማኝ ይሆኑልናል፡፡ ራሳችን ታማኝ ባልሆንበት ሁኔታ ከሰዎች ታማኝነትን መጠበቅ ቂልነት ነው፡፡ለትዳር አጋሮቻችን ለጓደኞቻችን ለቤተሰባችን ለአለቆቻችን ታማኝ ስንሆን ነው ከሰው ታማኝን ልናገኝ የምንችለው፡፡
ታማኝነት በተግባር የሚገለፅ እሴት ነው፡፡ እያንዳንዳችን ምን ያህል ለራሳችን ታማኝ ነን ? ምን ያህልስ የምንሰራለትን አላማ ለማሳካት የተቻለንን ሁሉ እንጥራለን ? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያሳዩንን የአመራር ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ይህን ከማድረግ አንቆጠብም፡፡ታማኝነት የተስተካከለ ቤተሰብ ለመመስረትም ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ለቤተሰባችን ፍቅር መስጠት ከታማኝነት መገለጫዎች ነው፡፡አላህ (ሱ) በተከበረው ቁርአኑ ወላጆቻችን አጋሪዎች ቢሆኑ እንኳን አለማዊ ህይወታቸው አጋር እንድሆናቸው አዞናል፡፡

3.ነብያዊ የአመራር ራእይ (Vision)

አላህ (ሱ) ለነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) በ40 አመታቸው የእስልምና ተልእኮ አስጨብጦና ራእይ ቀርፆ መልእክተኛ አድርጓቸዋል ፡፡ ከዚያም ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ተልእኮ ተረድተው ፤ተርጉመውና በተግባር መሬት ላይ ተግብረው አሰይተውናል፡፡ ለብዙ መሪዎች አስቸጋሪ መሰናክል ራእይን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መለወጥ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቀላሉ ተተግብሯል፡፡ አንድን ተልእኮ ማሳካትና ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ራእይ መቅረፅ አስፈላጊ ነው፡፡ ባለራእዮች ተልእኳቸውን ለማሳካት የሚረዱ የተለያዩ መንገዶችን መሰናክሎችና መልካም አጋጣሚዎች አስቀድመው መገመት ይችላሉ፡፡እያንዳንዱ አስቸጋሪ የህይወት አጋጣሚ እንዴት ማለፍ እንዳለባቸው መመዘኛ የሚሆን መስፈርት ከራእዩ ያገኛሉ፡፡
በስድስተኛው አመተሂጅራ የተደረገው ሁደይቢያ ስምምነት የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ባለራእይነት አርቆ አሳቢነት አጉልቶ ካሳዩ ክስተቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በስምምነቱ ላይ ምንም እንኳን በዚያ አመት ወደ መካ መግባት ቢከለከሉም ለአስር አመት የሚዘልቅ የሰላም ስምምነት ለማግኘት ችለዋል፡፡ይህ ከችግር ውስጥ ምርጥ መፍትሄ የማውጣት ችሎታ ነው፡፡በወቅቱ ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ውስጥ ትልቁን ስዕል ማየት ያልቻሉቱ በስምምነቱ ቅር ተሰኝተው ነበር፡፡ነገር ግን ሁደይቢያ ስምምነት በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ባለራእይነት አርቆ አሳቢነት ምክንያት በኢስላም ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ትቶ ማለፍ የቻለ ታላቅ ድል ሆኖ አልፏል፡፡
የግል ህይወታችንንም ቢሆን በእቅድ ልንመራ ይገባል፡፡ የህይወት ግብ ሊኖረን ይገባል:: ህይወትን በተፃፈ እቅድ መምራት ለስኬት መሰረት ነው፡፡ ባለራእይ ልንሆን ይገባል፡፡ታሪካችንን ወደ ኋላ በመገምገምና አሁን ያለንበትን ሁኔታ በማገናዘብ የወደፊት ህይወታችንን አቅጣጫ ማስያዝ ለነገ የማይተው ስራ ነው፡፡ ሰዎች እቅዳቸውን የአመት የአምስት አመትና የአስር አመት በሚል በሶስት ደረጃዎች ማውጣት የተሸለእንደሆነ የዘርፍ ጠበብት ይመክራሉ፡፡ በእቅድ መመራት በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ የትዳር አጋራችንን ስንመርጥ ራእያችን ከአጋራችን ራእይ ጋር ሊጣጣም ይገባል፤ ሁለት የሚጣረስ የህይወት ራእይ ያላቸው ሰዎች ትዳር መስርተው መኖራቸው ትርጉም ላይሰጥ ይችላልና፡፡ እያንዳንዳችን የአላህ (ሱ.ወ) ፍቃድ ሆኖ በህይወታችን ምን ማድረግ እንደምንፈልግ ልናውቅና ለተግባራዊነቱ ልንንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ያለዚያ አንድ አዋቂ እንደሚሉት በምድር ላይ ምንም ነገር ሳንጨምር ምድር ላይ የኖርን ጭማሪዎች ሆነን እናልፋለን፡፡አላህ (ሱ.ወ) ይጠብቀን፡፡

4. ነብያዊ የአመራር ት፤ ራተጂ (Strategy)

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አመራር እጅግ የረቀቀ ስልታዊነት ይስተዋልበት ነበር፡፡ ይህም ባልደረቦቻቸውን(ረ.ዐ) ለተለያዩ ሀላፊነቶች በሚያጩበት ጊዜ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ለሀላፊነቱ የሚገባና የሚመጥን ሰውን መርጠው የመሾም ልዩ ብቃት ነበራቸው፡፡አምር ኢብኑ አስ ከሰለመ ከጥቂት ወራት በኋላ የጦር አዛዥ ሆኖ በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ተሹሟል(አምር በኢስላም ታሪክ ከበሳል መሪዎች ተርታ እንደሆኑ ልብ ይሏል)፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኡሁድ ዘመቻ የነበረውን ጀግንነትና ብቃት በሚገባ በማጤናቸው ለዚህ ሹመት አብቅተውታል፡፡ ከዚህ ክስተት የምንማራቸው በርካታ ፍሬዎች አሉ፡፡ ሰዎችን ለሃላፊነት ስንመድብ እድሜ የስራ ልምድ የግዜ ቆይታ እና የመሳሰሉትን ማየት አስፈላጊ ቢሆንም ዋነኛው መስፈርት መሆን ያለበት የግለሰቡ ለሃላፊነት የሚመጥን ብቃትና ችሎታ መሆኑን እንማራለን፡፡

5.ነብያዊ የአመራር ግለሰብ ተኮር አመራር (Transformative)

በዘመናችን ሁለት አይነት የአመራር አስተሳሰቦች አሉ፡፡የመጀመሪያው ተግባር ተኮር (transactional) አመራር ነው፡፡ይህ የአመራር አይነት የሚያተኩረው አንድን ተግባር በመፈፀም ላይ ነው፡፡ይህን ተግባር ስለሚፈፅሙት ሰዎች ሳይሆን ስለሚፈፀመው ተግባር ትኩረቱን ይሰጣል:: ሁለተኛውና የተመረጠው የአመራር አይነት ደግሞ ግለሰብ ተኮር(transformative) አመራር በመባል ይታወቃል ፡፡ ይህ የአመራር አይነት ስለሚፈፀመው ተግባር ከማተኮሩ ጎን ለጎን የሚፈፅሙት ግለሰቦች ማብቃት ላይ ጥረት ያደርጋል ፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተመራጭና  ግለሰብ ተኮር አመራር ተከትለዋል፡፡ የእስልምና መልእክት ለሰዎች የማድረስ ከባድ ተግባራዊ ተልእኮ ቢኖርባቸውም ይህን ተልእኮ ባልደረቦቻቸውን በማብቃት ወደ ስኬት እንዲደርስ አድርገዋል፡፡
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የሰዎችን መልካም ባህሪይ ለማሟላት መላካቸውን ሲነግሩን ይህን ሰው ተኮር አመራር እንደነበር ያሳያል ፡፡ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተገባር ተኮር መሪ ሆነው እያንዳንዱ ስራ በተገቢው መልኩ መፈፀሙን ብቻ የሚቆጣጠሩ መሪ አልነበሩም ይልቁንስ እንደ አሰልጣኝና መካሪ ሆነው ባልደረቦቻቸው ስራዎች በተገቢው መልኩ መስራት እንዲችሉ ለማብቃትና ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል በተግባርም ረድተዋል፡፡ እኛም በያለንበት የአመራር ቦታ ይህን ሰው ተኮር አምራር ዘዴ ልንከተል ይገባል፡፡