ሀዲሶች

የሐዲስ ዓይነቶች

የሐዲስ የጥናት መስክ “ሙሰጦለህ አል-ሐዲስ” ሀዲሶችን (ደረጃቸዉን መሰረት አድርጎ) የተለያዩ የሀዲስ አይነቶች እንዳሉ ያስተምራል። ከዚህ በታች የእያንዳንዱን ክፍል አሳጥረን እንመለከታለን።
  1. ሐዲሱ ከተወሰደበት ምንጭ አንጻር፡- ሀዲሱ የተወሰደዉ ቀጥታ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ)፣ ከሰሐባ ወይም ከታብዒይ ሊሆን ይችላል። ከዚህ አንጻር ሐዲሱን በቀጥታ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የመጣ ከሆነ (መርፉዕ) ሲባል ከሰሀባ የተወሰደ ከሆነ የቆመ (መውቁፍ) ተብሎ ሲጠራ ከታቢዒይ ከተወሰደ የተቆረጠ (መቅጡዕ) ይባላል።
  2. ከመረጃዎ ሰንሰለት አንፃር (ኢስናድ)፡- ይህ ማለት ደግሞ የመረጃ ሰንሰለት የተቋረጠ ወይም የተቀጠለ መሆኑን የሚያመለክት ነው። ከዚህ አንጻር የመረጃው ሰንሰለት (ኢስናድ) ሰንሰለቱ የተደገፈ (ሙስነድ)፣ ቀጣይነት ያለውን (ሙተሲል)፣ የተቆረጠ (ሙንቀጢዕ)፣ የተንጠለጠለ (ሙዓለቅ)፣ የተምታታ (ሙዓደል) እና የመረጃው ሰንሰለ የተዘለለ ከሆነ- ከታቢዒይ ተነስቶ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ የደረስውን (ሙርሰል) ይባላል።
  3. በእያንዳንዱ የመረጃ ሰንሰለት ሐዲሱን ከሚያስተላልፉት ሠዎች ቁጥር አንፃር፡- ሐዲሱ በብዙ አቅጣጫ ከተዘገበ ተከታታይ (ሙተዋቲር) ሲባል ከአንድ አቅጣጫ የተዘገበ ከሆነ ደግሞ ነጠላ (አሀድ) ይባላል። ነጠላ (አሀድ) በ ሶስት ይከፈላል። እነሱም እንግዳ (ገሪብ) መጠነኛ፤ ጠንካራ (ዐዚዝ) ታዋቂ (መሽሁር) ይባላል።
  4. ከሐዲሱ አዘጋገብ ሁኔታ አንፃር፡- ሐዲሱ “ከእገሌ” (ዓን) ተረከልን (ሐደሰና) ሐዲሱን ዘጋቢው ለተቀባዮቹ ሲተረክላቸው ደግሞ ነገረን (አኽበረና) ሐዲሱን ዘጋቢዉ ከሰማ (ሰሚዕቱ) ይላል። በተጨማሪም በዚህ የሐዲስ ሰንሰለት አዘጋገብ ስር ስለተደበቀ (ሙደለስ) እና ወጥ (ሙሰልሰል) የሀዲስ አይነቶችን ማየት ይቻላል።
  5. ከሐዲሱ ጥሬ መልዕክት (መትን) እና ከመረጃው ሰንሰለት (ኢሰናድ) አኳያ፡- በሐዲሱ ላይ የታማኝ ዘጋቢ ጭማሪ (ዚያደቱል ሲቃ) ይባላል። ታአማኒነቱ ዝቅ ያለው ዘጋቢ ታማኝ የሆነዉን ዘጋቢ ሲቃወም ኢ-መደበኛ (ሻዝ) ይባላል። በአንዳንድ ሁኔታም ግልፅ እና ምንክያታዊ ያልሆነ መልዕክት የያዘ ሀዲስ በሐዲስ አዋቂዎች ዘንድ “ሰነዱን” ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ሀዲሱን ውድቅ ያደርጉታል። የዚህ አይነቱ ሐዲስ ተቀባይነት የሌለው (ሙንከር) ይባላል። ከዋናው የሐዲስ ገለፃ ላይ በዘጋቢዉ የሚጨመር ተጨማሪ ሀሳብ ደግሞ የተበረዘ (ሙድረጅ) ይባላል።
  6. በሐዲሱ ሰነድ ወይም መትን ረቂቅ እንከን ከመኖር አኳያ፡- ከላይ በተዘረዘሩት የሐዲስ አይነቶች ውስት ሊካተት ቢችልም ነጥሎ ማየቱ አይከፋም። ረቂቅ እንከን ያለበት በሽተኛ (ሙዐለል) ይባላል። ሐዲሱ ላይ የሚከሰተዉ እንከን የተለያየ ሊሆን ቢችልም በሽተኛ (ሙዐለል) ሀዲስ ሁለት አይነት መልክ አለዉ፤ እነሱም የተገለበጠ (መቅሉብ) እና የሚያጠራጥር (ሙጦሪብ) ናቸዉ።
  7. ከዘጋቢው ታማኝነትና አስተዋሽነት አንፃር፡- የሐዲሱ የመጨረሻ ውሳኔ ከዘጋቢው ታማኝነትና አስተዋሽነት አንፃር የተያያዘ ነው። ይህ ውሳኔም ሐዲስ እጅግ በጣም ትክክለኛ (ሶሒሕ)፣ መለስተኛ ትክክለኛ (ሐሰን)፣ ደካማ (ዶዒፍ) እና መሰረተ-ቢስ (መውዱዕ) ተብሎ እንዲከፈል ያደርጋል። ብዙ ጊዜ እነዚህ የሐዲስ አይነቶች መሰረት የሚያደረጉት ኢስናድ ላይ ያለውን የዘጋቢውን ሚና ከግምት ዉስጥ በማስገባት ነው።

የሐዲስ አስፈላጊነት በእስልምና

ሐዲስና ቁርአን የማይነጣጠሉ አንድ አካል ናቸው። የሐዲስ መረጃዎችን ሳናጣቅስ ቁርዓንን መረዳት ፈፅሞ አዳጋች ነው። ቁርዓን በጅብሪል (ዐ.ሰ) አማካኝነት ከአላህ (ሱ.ወ) የመጣ መልዕክት ሲሆን ሐዲስ (የነብዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ንግግሮች፣ ተግባራትና አጠቃላይ ህይወት) ደግሞ የዚህ መልዕክት ማብራሪያ ነው። ይህንን ሀሳብ የሚከተሉት አራት ነጥቦች ያጠናክሩልናል።

1. ቁርዓን በበርካታ አንቀፆች ላይ በግልፅ እደሚያሰወቀምጠው የመልዕክተኛው ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ተግባር መልዕክቱን (ቁርዓንን) ማድረስ ብቻ እንዳልሆነ እንረዳለን። ይልቁንም መልዕክቱን የማብራራትና ግልፅ የማድረግ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው ነው የተላኩት።
ይህ ሀሳብ በበርካታ የቁርዓን አንቀፆች ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ለምሳሌ፡- አል-ነህል 16፤44 እንዲሁም አል-ነህል 16፤64 መጥቀስ ይቻላል።
وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ [١٦:٤٤]
“ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡” (አል-ነህል 16፤44)
وَمَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ الَّذِي اخْتَلَفُوا فِيهِ وَهُدًى وَرَحْمَةً لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ [١٦:٦٤]
“ባንተም ላይ መጽሐፉን አላወረድንም፤ ያንን በርሱ የተለያዩበትን ለነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ሕዝቦች መሪና እዝነት ሊኾን እንጂ፡፡” (አል-ነህል 16፤64)
ስለዚህ ከላይ ከተጠቀሱት የቁርዓን አንቀፆች የምንረዳው ነገር፣ ሐዲስ ቁርዓንን ግልፅ ከማድረግ እና ከማብራራት በዘለለ በቁርዓን ላይ ያሉ ብዥታዎችን የማጥራት ሚና ይጫወታል። ስለሆነም ሐዲስን ወደጎን በመተው የቁርዓንን አጠቃላይ መልዕክት ለመረዳት መሞከር ፍፁም የማይቻል ነገር ይሆናል።
2. ያለሐዲስ ተጨማሪ ማብራሪያ አብዛኛዎቹ የእስልምና አስተምህሮዎች ከወረቀት ፅሁፍነት የዘለለ ሚና አይኖራቸውም። ምክንያቱም ያለሐዲስ እንዴት መስገድ፣ መፆም፣ ዘካ ማውጣት እንዲሁም ሀጅ ማድረግ እንዳለብን አናውቅም። እነዚህን የአምልኮ ግዴታዎች በደፈናው ተቀመጡ እንጂ በቁርዓን ውስጥ እንዴት ለሚለው ጥያቄ ሰፋ ያለ ምላሽ አናገኝም።
3. አላህ (ሱ.ወ) በቁርዓኑ እንደሚነግረን ከሆነ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለተከታዮቻቸው ያስተማሩት ቁርዓኑን ብቻ ሳይሆን ጥበቡንም (ሒክማ) ጭምር ነው። ይህን በተመለከተ በቁርዓን ውስጥ 2:231፣ 33፡34፣ 4፡113 እና ሌሎችንም መመልከት ይቻላል።
وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمَا أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنَ الْكِتَابِ وَالْحِكْمَةِ يَعِظُكُم بِهِ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ [٢:٢٣١]
“የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን ከመጽሐፍና ከጥበብም በርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በናንተ ላይ ያወረደውን አስታውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን ዕወቁ፡፡” (አል-በቀራ 2፤231)
وَاذْكُرْنَ مَا يُتْلَىٰ فِي بُيُوتِكُنَّ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ وَالْحِكْمَةِ إِنَّ اللَّهَ كَانَ لَطِيفًا خَبِيرًا [٣٣:٣٤]
“ከአላህ አንቀጾችና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ፡፡ አላህ እዝነቱ ረቂቅ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡” (አል-አህዛብ 33፤ 34)
وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا [٤:١١٣]
“አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡” (አን-ኒሳእ 4፤ 113)
እንደ ኢማሙ ሻፊዒ አባባል ከሆነ “ጥበብ” ሲል አላህ (ሱ.ወ) የገለፀው የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ወይም ሱናን ነው። እናም ሐዲስን መተው (ችላ ማለት) ቁርዓንን እንደመተው (ችላ እንደ ማለት) ሊቆጠር ይችላል።
4. ቁርዓን ሁሌም መልዕክተኛውን (ሰ.ዑ.ወ) እንድንታዘዝና መመሪያቸውን እንድናከብር በተለያዩ አንቀፆች ገልፆልናል። ተከታዮቹ አንቀጾች ለዚህ ምሳሌ ይሆኑናል፡-
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا [٤:٦٥]
“በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡” (አን-ኒሳዕ 4፤65)
وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ وَاحْذَرْهُمْ أَن يَفْتِنُوكَ عَن بَعْضِ مَا أَنزَلَ اللَّهُ إِلَيْكَ فَإِن تَوَلَّوْا فَاعْلَمْ أَنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ أَن يُصِيبَهُم بِبَعْضِ ذُنُوبِهِمْ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ لَفَاسِقُونَ [٥:٤٩]
“በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ ፍላጎቶቻቸውንም አትከተል፡፡ አላህም ወደ አንተ ካወረደው ከከፊሉ እንዳያሳስቱህ ተጠንቀቃቸው (ማለትን አወረድን)፡፡ ቢዞሩም አላህ የሚሻው በከፊሉ ኃጢአታቸው ሊቀጣቸው መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡” (አል-ማዒዳህ 5፤49)
ታዲያ ይህን መሰል ትዕዛዛት (ውሳኔዎችን) ከሐዲስ ውስጥ ካልሆነ የት ልናገኛቸው እንችላላን?
ቁርዓን ሙእሚኖችን መልክተኛውን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው አርአያ አድርገው እንዲይዙና ይህም የአላህን ውዴታ ለማግኘት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ይገልፃል። ስለዚህ በዘወትር እንቅስቃሴያችን የመልዕተኛውን ባህሪያትና ተግባራት ማንፀባረቅ በእጅጉ አስፈላጊ ይሆናል። ይህንን ልናደርግ የምንችለው ደግሞ ሐዲን በአግባቡ ማጥናት ስንችል ነው።
ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ስለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ባህሪ በተጠየቀች ግዜ የሰጠችው መልስ ይህን ጉዳይ በደንብ ያብራራልናል። ስለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የተናገረችው እንዲህ ብላ ነበር “ባህሪያቸው ቁርዓን ነበር” ይህ ማለት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የቁርዓን ፅንስ ሃሳቦችንና እሴቶችን በተግባር አንፀባርቀዋል እንደማለት ነው። ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ቁርዓናዊ ሀሳቦች ግልፅ የተደረጉበትን እና ወደ ነብዩ ህይወት ሊመሩን የሚችሉትን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ገሸሽ የምናደርገው? ይህን ስንል ግን አንድ ልንረዳው የሚገባ ነጥብ አለ ይኸውም ሁሉም የሐዲስ ስብስቦች እውነተኛ እና ቅን ናቸው ማለታችን አይደለም። ሐዲሶች ሁሌም ቢሆን ታላላቅ የኢስላም ምሁራን ባስቀመጧቸው መመዘኛዎች መገምገም አለባቸው። ከመመዘኛዎቹ ውስጥ ከመሠረታዊ የቁርዓን መርህ ጋር ወይም ግልፅ ከሆነ ዕውነታ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ምንጩ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስለማይሆን እንደ ሀዲስ አይወሰድ፡፡
                                                                                                                                                                                                         1) አነስ 
(ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
«የሶስት ነገሮች ባለቤት የሆነው ሰው የእምነትን ጣዕም ያገኛል፡፡
1. አላህንና መልዕክተኛውን ከሌላ ወገን ይበልጥ ከርሱ ዘንድ ተወዳጅ ያደረገ፤
2. ሰውን የሚወድ (ግና) የሚወደው ለአላህ ብቻ ሲል የሆነ፡፡
3. እሳት ውስጥ መግባትን እንደሚጠላ ሁሉ ወደ ክህደት (ኩፍር) ውስጥ መመለስን ጠልቶ ሲገኝ፡፡»

2) “እያንዳንዱ መልካም ተግባር ሰደቃ ነው።”
      ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) (ቡኻሪና ሙስሊም)

3) ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ምንም አይነት የሚያስከፋና አሳዛኝ ዜና ሲሰሙ፦ "አልሃምዱ ሊላህ አላ ኩሊ ሃሊን"
     በሁሉም ነገር (ጥሩም ሆነ መጥፎ) ለአላህ ምስጋና ይገባው ይሉ ነበር::

4) ረሱል(ሰ.ዐ.ወ)<የተራበን መግብ የተጠማን አጠጣ ሰዎች መልካም እንዲሰሩና ከመጥፎም እንዲከለከሉ እዘዝ ይህን
     ማድረግ ካልቻልክ ምላስህ መልካም ይናገር አለዝያ ዝም በል ! >>

5) “ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣና የአላህን ትዕዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ
       እደወለደችዉ ቀን ከኃጢአቶቹ ጠርቶ ይመለሳል፡፡” ነቢዩ (ሰዐወ)

6) አንድ፡ሙስሊም፡አንድም፡ችግር፣በሽታ፣ስጋት፣ቁጭት፣አዋኪ፡ነገርም፡ሆነ፡ጭንቀት፣እሾህ እራሱ፡ቢወጋው፤
    በሚገጥመው፡ሁሉ፡አላህ፡ኃጢአቱን፡ያብስለታል(ይምረዋል)።ነብዩ (ሰዐወ) /ቡኻሪና ሙስሊም/

7) “ኢማን ከ 73 እስከ 79 ወይም ከ 63 እስከ 69 የሚደርሱ ቅርንጫፎች አሉት። ከፍተኛውና በላጩ «ላኢላሀ ኢልለላህ»ን ማለት
    (ከአላህ ሌላ የሚመለክ ኃይል እንደሌለ መመስከር) ሲሆን፣ የመጨረሻውና ዝቅተኛው ከመንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ ነው።
     «ሐያእ» የኢማን አንዱ ዘርፍ ነው።” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) /ቡኻሪና ሙስሊም/

8) “ጠንካራ ሙዕሚን ከደካማ ሙዕሚን በላጭና ከአላህ ዘንድም ይበልጥ ተወዳጅ ነው። ሁሉም መልካም ቢሆኑም። የሚጠቅምህን
     ለመፈፀም ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ፤ አትስነፍ። አንዳች (ክፉ) ነገር ሲገጥምህ፦ <ይህን፥ ይህን አድርጌ ቢሆን ኖሮ (ይህ ነገር
    አይደርስብኝም ነበር)> አትበል። ይልቁንም <አላህ የወሰነው ነገር ተፈፃሚ ሆነ፤ የአላህ ፍላጎት ተሟላ፤> «በል» (ቢሆን ኖሮ)
    የሰይጣንን ሥራ ትከፍታለችና” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) /ሙስሊም/

9) “ሰባት (ፈታኝ ሁኔታዎች ሳይገጥማችሁ በፊት) ለመልካም ተግባራት ተሽቀዳደሙ። ወደፊት የሚመጠብቃችሁ አዘናጊ የሆነ ድህነት፣
     ወይ ለአመጽና ወንጀለኝነት የሚዳርግ ሀብት፣ በካይ የሆነ በሽታ ወይም የሚያጃጃ እርጅና፣ አጣዳፊ ሞት፣ ክፉው ይመጣል ተብሎ
     የሚጠበቀው ደጃል ወይም ወሰን የለሽ መከራና አስከፊ ቅጣት የሚከሠትበት ዕለተምፅዓት (ቂያማ) ነው።” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) /ቲርሙዚይ/

10) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡
      ዐዋቂና ብልህ ሰው ማለት ሥጋዊ ፍላጎቱንና ስሜታዊ ዝንባሌውን ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ የሰራ ነው። ሞኝ ተላላና ደካማ
      ሰው ማለት ደግሞ ራሱን (ወደ ተከለከሉና አጥፊ ወደሆኑ እኩይ ተግባራት በምትመራው ነፍሱ) ስሜታዊ ዝንባሌ ቁጥጥር ሥር አውሎ
     የዝንባሌው ተከታይ በመሆን (ምህረትና ጸጋውን ያላንዳች ጥረት) በባዶ ተምኔት ከአላህ የሚጠብቅ ሰው ነው። /ትርሚዚ/

11) “አላህ ደግ የሻለትን ሰው በአንድ ነገር ይፈትነዋል።”
       የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) /ቡኻሪና ሙስሊም/

12)“ለዱንያውም ሆነ ለአኺራው የማይጠቅመውንና የማይመለከተውን
      ነገር መተው ለአንድ ሰው የመልካም ሙስሊምነቱ አንድ መገለጫ ነው።”
       ነብዩ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) /ትርሚዚና ሌሎችም የዘገቡት ሃዲስ/

13) “ባለህበት ቦታ ሁሉ አላህን ፍራ (በትክክል ተገዛው)።
        ክፉ ሰርተህ ከሆነ ወዲያውኑ መልካም ስራ አስከትልበት፤
        ያብሰዋልና። በመልካም ስነምግባር ከሰዎች ጋር ኑር።” የአላህ መልዕክተኛ
        (ሰ.ዐ.ወ) /ትርሚዚ የዘገቡት/

14) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡ “…ሙዕሚን(አማኝ ሰው) ነገሩ ሁሉ አስደናቂ ነው። ነገሩ ሁሉ መልካም ነው። ይህ ደግሞ ማንም
      ሊያገኘው ያማይችል እና ለሙዕሚን ብቻ የተወሰነ ነው። ጥሩ ከገጠመው ያመሰግንና አጅር ያገኛል። መጥፎ ከገጠመው ደግሞ፣
      ይታገስና የታጋሾችን አጅር ያገኛል።” (ሙስሊም)

15) ረሱል(ሰ.ዐ.ወ.) ረመዳን ካሉት ፈዳኢልችና በረከቶች ዋና ዋናዎቹን በሚጠቅሱበት ሀዲሳችው ውስጥ እንዲህ ይላሉ “መጀመሪያው እዝነት፤
     መካከለኛው ምህረት፤ መጨረሻው ደግሞ ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት ነው።” ማለትም በመጀመሪያ አስር ቀናቶች አላህ (ሱ.ወ) ለትክክለኛ
      ባሮቹ እዝነቱን ያርከፈክፍባቸዋል፡ በሁለተኛው አስር ቀናቶች ደግሞ ምህርቱን ይለግሳቸዋል፡ በመጨርሻም አስርት ቀናት እነዚን
       ጿሚዎች ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት ይሆናል።

16 )  ከውዱእ ቡኋላ የሚከተልውን ዚክር ያለ ሰው ስምንቱ የጀነት መግቢያ በሮች ተከፍተውለት በፈለገው በር ይገባል። (ሙስሊም እና ቲርሚዚ)

17) ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)፦ “ከሥራችሁ ሁሉ ብላጭ ይሆነ፥ ወርቅና ብር ከምትለግሱ የተሻለ ምንዳ የሚያስገኝላችሁና ከጠላት ጋር ተገናኝታችሁ አንገታችሁን ከመሞሻለቅ የበለጠ
ሥራ ልጠቁማችሁን?” በማለት ጠየቁ። “አዎ” አሏቸው። “አላህን ማውሳት” በማለት መለሱ። (ቲርሙዝይና ኢብን ማጀህ)”

 18) የአላህ መልዕክተኛ ከሺህ አራት መቶ ዓመታት በፊት እንዲህ ብለው ነበር፡- ‹‹ከእናንተበፊት የነበሩትን (ሕዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ።የፍልፈል (ወከሎ) ጉድጓድ ቢገቡ እንኳ (ተከትላችሁ) ትገባላችሁ!›› ሰሃቦችምእንዲህ አሉ፡- ‹የሁዶችንና ክርስቲያኖችን?› ረሱልም፡- ‹(ታዲያ) ማንን?›አሉ። ከካፊሮች ጋር መመሳሰል ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው።‹‹ከሕዝቦች ጋር የተመሳሰለ ከእነሱ ነው›› ብለዋል መልዕክተኛው።ስለዚህ ከዲን መሰረት በሌለው ነገር ካፊሮችን መፎካከር አይኖርብንም።አሏህ ከመመሳሰል ይጠብቀን

19) የዙልሂጃ አስር ቀናት የአላህ መልዕክተኛ (ሱ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ አላህ ዘንድ መልካም መስራት ይበልጥ ተወዳጅ የሆኑበት ቀናት ቢኖር እነኝህ ናቸው የዙልሂጃ የመጀመሪያው አስር ቀናት ሶሀባዎች ጠየቁ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ጂሐድ ፊሰቢሊላህ እንኳ ቢሆን አዎ ጂሐድ ፊሰቢሊላህ እንኳን ቢሆን በነኝህ አስር ቀናት ከመፆም የበለጠ ዋጋ የለውም ነገር ግን በነፍሱና በገንዘቡ ጂሐድ ተሳትፎ ወደ ቤቱ ያልተመለሰ ሰው ሲቀር.

20) ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:_ "አላህን ጠቃሚ እውቀትን ጠይቁት ከማይጠቅም እውቀት በአላህ ተጠበቁ::" (ኢብን ማጃህ)

21) ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » አልበዛር እና አልሐይሰሚይ ዘግበዉታል አልባኒም ሰሂህ ብለዉታል (ሰሂሁል ጃሚዕ 1133

22)ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።»
 ቡኻሪ ዘግበውታል

23)ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡"ዐዋቂና ብልህ ሰው ማለት ሥጋዊ ፍላጎቱንና ስሜታዊ ዝንባሌውን ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ የሰራ ነው። ሞኝ ተላላና ደካማ ሰው ማለት ደግሞ ራሱን (ወደ ተከለከሉና አጥፊ ወደሆኑ እኩይ ተግባራት በምትመራው ነፍሱ) ስሜታዊ ዝንባሌ ቁጥጥር ሥር አውሎ የዝንባሌው ተከታይ በመሆን (ምህረትና ጸጋውን ያላንዳች ጥረት) በባዶ
ተምኔት ከአላህ የሚጠብቅ ሰው ነው።" /ትርሚዚ/ ጀነት መዳረሻው የሆነ ብልጥነት (ጮሌነት) አላህ የጎናጽፈን!

24) ነቢያችን(ሰ.ዐ.ወ) ሲናገሩ"እኔ የተላኩት የመልካም ሥን-ምግባራትን ዕሴት ላሟላ ነው"(አህመድ)::በሙስሊሞች መካከል ሊኖረው እሚገባው ግኑኝነት በቁሳዊ ጥቅም መመስረት የለበትም::ለአላህ(ሱ.ወ) ብሎ መዋደድ በዱንያም በአኺራም ምርጥ ህይወት የሚያስገኝ ነው::እውን እኛ ሙስሊሞች ለአላህ ብለን እንዋደዳለን? ሀሳባችሁን አካፍሉን...

25) ረሱሉ( ሰ`ዓ`ወ `)አቡሁረ ይራ በዘገቡት:ሐዲስ እንዲህ ብለዋል “በአላህና በ መጨረሻው ቀን የሚያምን ጥሩን ይናገር:ካልሆነ ዝምይበል“: “በአላህና በ መጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቢቱን ያክብር : “በአላህና በ መጨረሻው ቀን:ያመነ :እንግዳ ዉን :ያክብር:

26) ከነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደተላለፈው ከኡምራ እስከ ኡምራ ወንጀል ይታበሳል። ትክክለኛ ሐጅ (አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይሆንም።

27) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)“ባለህበት ቦታ ሁሉ አላህን ፍራ (በትክክል ተገዛው)።
ክፉ ሰርተህ ከሆነ ወዲያውኑ መልካም ስራ አስከትልበት፤ያብሰዋልና። በመልካም ስነምግባር ከሰዎች ጋር ኑር።” የአላህ መልዕክተኛ
(ሰ.ዐ.ወ) /ትርሚዚ የዘገቡት/

28)ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሲናገርኡ "አንድ ሰው ሲሞት ከሦስት ተግባራቱ በስተቀር ሁሉም ሥራዎቹ ይቆማሉ
1.ቋሚ ነገርን ያቋቋመ(ሰዎች እሚጠቀሙበት)
2.ጠቃሚ እውቀት የተወ
3. ዱዓ የሚያደርጉለት መልካም ልጆችን ያሳደገ:: (ሙስሊም)

29) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት (ጠንካራ ሙዕሚን ከደካማ ሙዕሚን በላጭና ከአላህ ዘንድም ይበልጥ ተወዳጅ ነው። ሁሉም መልካም ቢሆኑም የሚጠቅምህን ለመፈፀም ጉጉት ይኑርህ።
በአላህ ታገዝ አትስነፍ። አንዳች (ክፉ) ነገር ሲገጥምህ ይህን ይህን አድርጌ ቢሆን ኖሮ (ይህ ነገር አይደርስብኝም ነበር) አትበል። ይልቁንም "አላህ የወሰነው ነገር ተፈፃሚ ሆነ
የአላህ ፍላጎት ተሟላ" በል (ቢሆን ኖሮ) የሰይጣንን ሥራ ትከፍታለችና) ሙስሊም

30) አንዲት ምዕራፍ አለች 30 አንቀጽ የሆነች ባለቤተዋን (አዘውትሮ የሚያነባትን) የምታማልድና ከወንጀሉ የምታስምር (እረሱዋም) ተባረከለዚ ቢየዲሂልሙልክ

31) "ሰዎች ሆይ ! ከዚህ ዓመት ብሁዋላ በመካከላችሁ እንደገና ለመገኘት መብቃቴን አላውቅምና ልብ ብሎ የሚያዳምጥ ጆሮ አዉሱኝ።ዛሬ የምናግራቺሁን ቁም ነገር በጥሞና አድምጡ።በዕለቱ
ከመካከላችሁ ለመገኘት ዕድል ላልገጠማቸው መልክቴን አድርሱ።ሰዎች ሆይ! ያዛሬው ወር፣የዛሬው ቀን፣ይህች ከተማ የተቀደሱና የተከበሩ መሆናቸውን የምታውቁትን ያህል የእያንዳንዱን ሙስሊም
ሕይዎትና ንብረት በክብር እንድትይዙ አደራ ተጥሎባችሁዋል።በእጆቻችሁ የሚገኙ የ አደራ እቃዎች ለባለቤቶቻቸው መልሱ።ማንም ሰው እንዳያጠቃቹ በማንም ሰው ላይ ጥቃት አታድርሱ።ያለምንም
ጥርጥር ፈጣሪያችሁ ፊት እንደምትቀርቡ አስታዉሱ።እርሱም ተግባራችሁን ይመዝናል።አራጣ እንዳትበሉ አላህ ከልክሎዋቺሁዋል።ስለዚህ ለመክፈል ቃል የገባችሁትን የብድር ወለድ መክፈል ከእንግዲህ
እርም ተደርጎባችሁዋል።ሃይማኖታቺሁን ለመከባከብ ከ ሰይጣን ተጠንቀቁ።በትልልቅ ጉዳዮች እናንተን አሳስቶ በዚህች ምድር ላይ (መካ)አዘቅት ዉስጥ ለመጣል በሚያደርጋው ሙከራ ተስፋ ስለቆረጠ
በጥቃቅን ጉዳዮች ሰይጣንን ተከታዮች እንዳትሆኑ ነቅታችሁ ጠብቁ።ሰዎች ሆይ! በሴቶቻችሁ ላይ የተወሰኑ መብት ያላችሁ መሆኑ እርግጥ ነው።ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብት አላቸው።በናንተ
ቁጥጥር ስር እስካሉ ድረስ የመመገብ፣የማልበስና በርህራሄ የመያዝ ግዴታ ይኖርባችሁዋል።ሴቶቻችሁ የኑሮ ጉአደኞቻችሁና የክርብ ደጋፊዎቻችሁ በመሆናቸው በርህራሄ አግባብ ባለው መልኩ ተንከባከቡዋቸው።
እናንተ ከማትፈልጉት ሰው ጋር ጉዋደኝነት እንዳይመሰርቱ ቤታችሁ በጭራሽ እንዳይደፈር ማድረግ የናንተ መብት ነው።ሰዎች ሆይ!በሚገባ አድምጡ ።አላህን ተገዙ።በቀን አምስት ጊዜ ሶላታችሁን ስገዱ።
የረመዳንን ወር ፁሙ።ከሀብታችሁም ዘካን ስጡለት።እንዲሁም ከተቻላችሁ ሃጅ አድርጉ።እያንድንዱ ሙስሊም ላሌላው ሙስሊም ዎንድም መሆኑን ታውቃላችሁ።ሁላችሁም እኩል ናችሁ።ማንም ሰው ካሌላው
የሚበልጥበት መንገድ የለም፣አላህን በመፍራት እና በጥሩ ምግባሩ እና ተግባሩ ቢሆን እንጂ!!!አስታዉሱ! አንድ ቀን በአላህ ፊት ቀርባችሁ ለሰራችሁት ስራ ትጠየቃላችሁ።ስለዚህ ተጠንቀቁ።
እኔ ካለፍኩ ብሁዋላ አልን ከመፍራት ጎዳና እንዳታፈነጊቱ።ሰዎች ሆይ! ከእኔ በሁዋላ አዲስ ነቢይ ወይም መልክተኛ አይመጣም።አዲስ እምነትም አይወለድም።በሚገባ ተመራመሩ።

32) ነቢያችን{ሰዐወ} እንዲ ብለዋል ከ አላህ ኪታብ አንድ ፊደል ያነበበ አንድ የመልክም ስራ ምንዳ {ሀሰና}ያገኛል አንዱ ሀሰና በ አስር ሊባዛለት ይችላል {አሊፍ ላም ሚም}
 አንድ ሆሄ ነው አልልም ፡፡ አሊፍ አንድ ሆሄ ነው ላም አንድ ሆሄ ነው ሚም አንድ ሆሄ ነው

33)ኢብን ቀይም (ረ ዐ) “ከእኔ በኋላ የምትመጡት ኡመቶቼ በርካታ ውዝግብ ይገጥማችኋል::እኔን ለምትከተሉት ግን የእኔ ሱንና በእናንተ ላይ ይሆናል”የሚለው የነብዩ (ሰ ዐ ወ) ሐዲሰ ሲተነትኑ:
 “ይህ ለእነዚያ እርሰ በርሳቸው ለሚወዛገቡት ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት ሲሆን እነርሱን ለሚከተሉም ማሰጠንቀቂያ ነው ይላሉ:: ጭፍን ክተላ ግላዊ ፍላጉቶችን ያሰከትላል::ይህ ደግሞ አለመግባባትንና
ክፍፍልን ይወልዳል::በመጨረሻም የመልዕክቶችን መበረዝ ያሰከትላል:: ይህ አንድ ነቢይ አንድ ወጥ ቁርአን እና አንድ አምላክ እያለን እንኳ የሚከሰት ነው::ሰለዚህ አላህ ያወረደውን ቁርኣን ነብዩ
(ሰ ዐ ወ) የተናገሩትንና ያከናወኑትን መከተል ከዚህ አይነት መከፋፈልና መፈራረጅ ያድነናል::ከአላህ መልክተኛ (ሰ ዐ ወ)ንግግሮች የሌሎች ሰዎችን ንግግር ማሰበለጥ ከአላህ ሌላ አምላክ ለማምለክ
ከመፈለግ መታቀብ የግድ ይሆናል:: በዚህ ከተሰማማን በነብዩ (ሰ ዐ ወ) በኩል የአላህን መልዕክት ሰንተገብር በነብዩ (ሰ ዐ ወ) ሱንና እና ከባልደረቦቻቸው ሱንና ላይ ተንተርሰን ሰንኖር ልዩነቶች
ሙሉ በሙሉ ባይከሰሙ እንኳን በእጅጉ ይቀንሣሉ::ለዚህም ነው በሱንና እና በሐዲሰ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ባሕሪያቸው ሥነ ምግባራቸውና ድርጊቶቻቸው በዚሁ ላይ ሰለሚታነጽ በመካከላቸው የሚኖረው
አለመግባባት እጅግ አነሰተኛ ሆኖ የምናገኘው:: ከሐቅ ራሱን ያራቀ ሰው ግራ ሰለሚጋባ እውነተኛው ሃይማኖት የትኛው እንደሆነና የት እንደሚያገኝው እርግጠኛ ሳይሆን ይቀራል::ቁርኣን “እውነትን
በመጥላታቸው ጊዜ አሰተባበሉ:: እነሱም ውዥንብር ውሰጥ ናቸው” ይላልና::

34)ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህመም ችግር አጋጥሞት ለሰው የማያማርር ሰው አላህ ሀጥያቱን ሁሉ ይምርለታል ብለዋል::

35) አብደላ ኢብነል አምር ኢብነል አስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ ሠው የአላህ መልእክተኛን (ሰ.ዐ.ወ)
/ከኢስላም መልካም ተግባራት/ ውስጥ በላጩ የትኛው ነው በማለት ጠየቃቸው:: ምግብ ማብላትህና
ለምታውቀውም ለማታውቀውም ሠላምታ ማቅረብህ ናቸው አሉት"

36) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)"የራስን ድክመት ሸፍኖ የሌሎችን ድክመት ከመፈለግ የከፋ ነገር የለም" ብለዋል::

37) ኢብን መስኡድ ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው ባወሩት ሀዲስ ከሀብት ሁሉ በላጩ የትኛው ነው ተብለው ሲጠየቁ አላህን የምታወሳ ምላስ; አመስጋኝ ልብ; ለአኼራ ጉዳይ አጋዥ የሆነች ሙእሚን ሚስት ናት ብለዋል::

38)ኢብን ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ኢማን ከስልሳ በላይ ንዑስ ክፍሎች አሉት፡፡ «ሐያእ» አንዱ የ«ኢማን» ንዑስ ክፍል ነው፡፡»
39)ዐብደሏህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ሙስሊም የሚባለው በምላሱና በእጁ ሙስሊሞችን ከመጉዳት የታቀበ (ነፃ የሆነ)
ሰው ነው፡፡ «ሙሃጂር (ስደተኛ) የሚባለው ደግሞ አላህ የከለከለውን ነገር ሁሉ የተወ ነው፡፡»

40)አቢ ሙሣ (ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የን ኢስላም በላጭነት አለው? (በጣም ጥሩ ሙስሊም ማን ነው)?» ተብለው ተጠየቁ፡፡ ሙስሊሞችን በምላሱና በእጅ የማይጐዳ»
የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

41)ዐብደሏህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዳወሱት አንድ ግለሰብ የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ በማለት ጠየቁ፡- «የማን ኢስላም የተሻለ ነው? (ወይም ከኢስላም መገለጫ
ባሕሪያት የትኞቹ የላቀ ደረጃ አላቸው?) «(ችግረኞችን) መመገብና በምታውቀውም ሆነ በማታውቀው ሰው ላይ ሰላምታ ማድረስ፡፡»

42)አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንዳችሁ እምነት ሊኖረው አይችል ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ፡፡»

43)አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ አመነ አይባልመ እኔን ከወላጁና ከልጁ በበለጠ ሁኔታ እስካልወደደ ድረስ፡፡»

45)አነስ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የሶስት ነገሮች ባለቤት የሆነው ሰው የእምነትን ጣዕም ያገኛል፡፡ አላህንና መልዕክተኛውን ከሌላ ወገን ይበልጥከርሱ ዘንድ ተወዳጅ ያደረገ፤ ሰውን የሚወድ (ግና) የሚወደው ለአላህ ብቻ ሲል የሆነ፡፡ እሳት ውስጥ መግባትን እንደሚጠላ ሁሉ ወደ ክህደት (ኩፍር) ውስጥ መመለስንጠልቶ ሲገኝ፡፡»

46)አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ከሥራው ሁሉ በላጩ የትኛው ነው?» የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ «በአላህና በመልዕክተኛው ማመን፡፡»አሉ፡፡ «ከዚያስ» ተባሉ፡- «በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጂሃድ ፊ ሰቢሊላህ)» በማለት መለሱ፡፡

47) አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የመናፍቅ ምልክቶች ሶስት ናቸው፡፡ ሲናገር ይዋሻል፤ ቃልኪዳን ሲገባ ያፈርሳል፤ሲታመን ይክዳል፡፡»

48)ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የገሃነምን እሶት እንዳየው ተደርጓል፡፡ከሓዲ ሴቶች በብዛት (የእሳት) ጓደኛ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡»« በአላህ ይክዳሉን?» የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡ ባሎቻቸውን ነው የሚክዱት፡፡ ለነርሱ የተዋለላቸውን መልካም ነገር ያስተባብላሉ፡፡ (ምስጋና ቢስ ይሆናሉ፡፡) ለብዙ ጊዜ ፀጋየዋልክላትን አንዲት ሴት ከዚያ ካንተ (የማትፈልገወን) አንድ ነገር ካየች «በምን አድርገህልኝ ታውቃለህ፡፡» ትላለች፡፡?»

49)አቡ ዘር (ረ.ዐ) እንዳሉት አንድን ሰው እናቱን በመጥፎ ስም በመጥራት አነወርኩት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉኝ፡- «አቡ ዘር ሆይ! በእናቱ አነወርከውን? አንተበውስጥህ የ«ጃሂሊያ» ባሕሪ ያለብህ ነህ፡፡ ባሪያዎቻቸሁ ሥር አድርጓቸዋል፡፡ ወንድሙ በእጁ ሥር የገባለት ሰው ከማበላው ይመግበው፣ ከሚለብሰው ያጐናጽፈው፣ የማችሉትንምነገር እንዲሠሩ አትጠይቋቸው፡፡ ይህን የምትፈጽሙ ከሆነ ግን እገዟቸው፡፡»

50)አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ዲን ገር ነው፤ አንድ ሰው በሃይማኖቱ (ክንውን) ላይ ከአቅሙ በላየ ከተሸከመ በዚሁ ሁኔታ
አይቀጥልም፡፡ ስለዚህ ፅንፈኛ አትሁኑ፡፡ ግን ወደ ፍጹምነት ለመቃረብ ሥራችሀን በጥራት ለማከናወን ጥረት አድርጉ፡፡ ሽልማት የምታገጉ በመሆኑም ደስታ ይሰማችሁ፡፡ በጧትም
ሆነ በማታ እንዲሁም በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ፀሎት በማድረግ ታገዙ፡፡ (የአላህን እርዳታ ፈልጉ)፡፡»

51)አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡- «የአንድን ሙስሊም ሙት አካል (ጀናዛ)» የሸኘ(መሸኘቱ ሐቅ መሆኑን አምኖና ዋጋ (አጅር)አገኝበታለሁ ብሎ በማሰብ እርሷ ላይ እስኪስግድባት ድረስና ተቀብሮ እስኪያልቅ ድረስ ከቆየ ሁለት «ቂራጥ» ምንዳ ይኖረዋል፡፡ እያንዳንዱ «ቂራጥ» ደግሞ የኡሑድ የሚያህል ነው፡፡ (በጀናዛው) ላይ የሰገደ ከዚያም ከመቀበሩ በፊት የተመለሰ አንድ «ቂራጥ» ይኖረዋል፡፡» ብለዋል፡፡

52)ዐብደላህ ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ሙስሊምን መሳደብ «ፉሱቅ» (መጥፎ ሥራ) ነው፡፡ መጋደሉ ደግመ «ኩፍር»(ክህደት) ነው፡፡»

53)አቡ መሰዑድ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንድ ሰው ለቤተሰቡ ወጭ ሲያደርግ ዋጋ አገኝበታለሁ ብሎ ካሰበ «ሶደቃ» ይሆንለታል፡፡»

54)ጀሪር ኢብን ዐብደሏህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው፡- «ለአላህ መልዕክኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሶላት ለመስገድ፤ ዘካ ለመስጠት፤ ለእያንዳንዱ ሙስሊም የምክር አገልግሎት ለመስጠት ቃልኪዳን ገብቻለሁ፡፡»

55) ሙአዝ ቢን አነስ (ረ.ዐ) የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ መናገራቸው ዘግበዋል "ከስራ ሁሉ በላጩ ዝምድና ያቁዋረጠብህን መቀጠል ለከለከለህ መስጠት ለበደለህ ይቅርታን ማድረግ ነው" ብለዋል::

56) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሲናገርኡ "አንድ ሰው ሲሞት ከሦስት ተግባራቱ በስተቀር ሁሉም ሥራዎቹ ይቆማሉ 1.ቋሚ ነገርን ያቋቋመ(ሰዎች እሚጠቀሙበት) 2.ጠቃሚ እውቀት የተወ 3. ዱዓ የሚያደርጉለት መልካም ልጆችን ያሳደገ:: (ሙስሊም)

57)እወቅ የሚያሳስትህ ሊጎዳህ አይደለም የሚጎህም ሊያሳስትህ አይደለም ድል (ውጤት) ያለ ትእግስት እፎይታ ያለ ችግር የተሻለ ነገር ከችግር ቦሀላ የሚገኙ መሆናቸውን እወቅ:: ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)

58) ነቢዩ ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል “አርብ ቀን ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ቅባትና ሽቶ ከተቀባ ቡሀላ ጁመዐ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደመስጊድ በመሂድ ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሽ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ ቡሃላ በፀጥታ ኹጥባውን ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመአ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሃጢአቱን አላህ የተውለታል

59)"በራስ መብቃቃትን የመሰለ እውቀት የለ ም፤ከሀራም መራቅን የመሰለ አላህን ፈሪነት የለም፤መልካም ባህሪ ማገኘትን የመሰለ ክብር የለም።" ረሱል (ሰአወ)

60) ረሱል{ሰ ዐ ወ} ከሰሃቦቻቸው ጋር ተቀምጠው እንዲ አሉ ‘’ወንድሞቼ ናፈቁኝ..” ሰሀቦቹም ‘’ያ ረሱል አላህ እኛ ውንደሞት አይደለን እነዴ?’’ብለው ሲጠይቋቸው ‘’አይ እናንተ ጓደኞቼ ናችሁ ውንደሞቼ ማልት እኔ ካለፍኩ ቡሀላ ሳያዩኝ በኔ ያመኑ.

61) ‎"አንድን ሙስሊም የሚያከብር በትህትና የሚያናግር, ሀዘኑን የሚያቃልል ሁሌም በአላህ በረካ ውስጥ ነው" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)

62)“ለዱንያውም ሆነ ለአኺራው የማይጠቅመውንና የማይመለከተውንነገር መተው ለአንድ ሰው የመልካም ሙስሊምነቱ አንድ መገለጫ ነው።”ነብዩ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) /ትርሚዚና ሌሎችም የዘገቡት ሃዲስ/

63)ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊም ነን የምትሉል ግን ዕምነት በውስጣቹ ያልገባ ሰዎች ሆይ:- በሙስሊም ላይ መጥፎን አተናገሩ ጉድለትን አትፈልጉ በሰውች ላይ ጉድለትን የሚፈልግ ሰው አላህም በሱ ላይ ጉድለትን ይፈልግበታል በሰዎች መሀልም ያዋርደዋል::

64)ፍጡርን ስትፈራው ትሸሸዋለህ አጋርነቱ ከሚሠማህ ይልቅ ብቻህን የሆንክ ይመስልሀል ፈጣሪን ስትፈራው ግን ከብቸኝነት ስሜት ትላቀቃለህ የርሱንም ቀረቤታ ትጨምራለህ:: ረሡል (ሰ.ዐ.ወ)

65)ብርቱ ሰው ማለት ታግሎ የሚጥል ሳይሆን ሲቆጣ ራሱን መቆጣጠር የሚችል ነው:: ረሡል (.ሠ.ዐ.ወ)

66)ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲ ብለውል” ከእያንዳንዳችሁ በር ላይ ወራጅ ወንዝ ቢ ኖርና አንድ ሰው ከዚያ ወንዝ በቀን 5ጊ ገላውን ቢታጠብ ቆሻሻ ይቀረዋልን ?ሶሀቦዎች መልስ ሰጡ “ምንም ቆሻሻ አይቀረውም’’ ነቢዩም 5 ወቅት ሰላት እንደዚሁ ነው አላህ (ሱ ወ) በእነርሱ ወንጀልን ያብስባቸዋል\
67)ነቢዩ {ሰ ዐወ} “እማ! ደህና ነሽ?” ብለው በጠየት ቁጥር የምትሰጠው ምላሽ {የ አላህ መልክተኛ ሆይ ኢስላም ደህና እስከሆነ ድረስ እንም ደህና ነኝ!’’የሚል ነበር {በረካ ረ.ዐ} { የጀነት ሲት ማግባት የሚሻ ሰው ኡሙ አይመንን {በረካን ያግባ} ነቢዩ {ሰ ዐወ}

68) አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የመናፍቅ ምልክቶች ሶስት
ናቸው፡፡ ሲናገር ይዋሻል፤ ቃልኪዳን ሲገባ ያፈርሳል፤ሲታመን ይክዳል፡፡»

69)ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ከሴቶቻችሁ በላጯ ቤቷ ውስጥ ሽቶ የምትቀባ: ጥሩ ምግብ የምታዘጋጅ: አላግባብ ወጪ የማታወጣ ናት 70)አቡ ሁራይራ እንደዘገቡት የ አላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፥ ”እኔ የእየሱስ በዚህ ዓለምም ሆነ በተከታዩ ዓለም እጅግ በጣም ቅርብ ወዳጁ ነኝ።ነብያት ወንድማማቾች ናቸው።አባታቸውም አንድ ሲሆን እናቶቻቸው ይለያያሉ።ሃይማኖታቸው ግን አንድ ነው። በእኔና በእየሱስ መካከል ሌላ ነብይ የለም።”(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል) 71)አቢ አብዱረህማን ዐብደላህ ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ)
የትኛው ሰራ ነው ከኣላህ ዘንድ ይበልጥ በላጭ (ተወዳጁ) በማለት ጠየኳቸው።
ሶላትን በወቅቱ መስገድ አሉኝ
ከዚያስ ቀጥሎ? አልኳቸው ።
ለወላጆችን በጐ መዋል አሉኝ።
ከዚያስ ቀጥሎ? አልኳቸው ።
በአላህ መንገድ መታገልአሉኝ
(ቡኻሪና ሙስሊም)

72)አቡ ሁረይራ (ረ ዐ) እንዳሰተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶ ዐ ወ) እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:
“ከበሂ እሰራኤሎች መካከል ሦሰት ሰዎች:አንደኛው ለምፃም ሌላኛው በራ ሦሰተኛው ደግሞ እውር አላህ ሊፈትናቸው ፈለግ::መላኢካ ላከባቸው::ለምፅ ያለበትን ሰው መጣና: “በጣም የምትወደው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው::”መልካም መልክ መልካም ቆዳ::ሰዎች እኔን እንዲጠየፉኝ ምክንያት የሆነው በሸታዬም እንዲወገድልኝ”ሲል መለሰ:: አበሰው መላኢካው:: አሰፀያፊው ሁኔታም ተወገደለት::መልካም መልክ ተሰጠ:: “ ከገንዘብ የትኛው ነው ካንት ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ” በማለት ጠየቀው:: (ግመል ወይም ላም”መለሰለት::እርጉዝ ግመል ተሰጠው:: “አላህ ይባርክልህ” ሲልም መረቀው:: ወደ በራው ሰውዬ በመሄድም በእጅግ የምትወደው ነገር ምንድን ነው? አለው:: መልካም ፀጉር ሰዎች እንዲፀየፉን ምክንያት የሆነው በራየም እንዲወገድ:አለ አበሰው በራው ተወገደለት:: ማራኪ ፀጉርም ተሰጠው:: ከገንዘብ የትኛው ነው ካንት ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ ሲል ጠየቀው:: ላም አለ::ያረገዝች ላም ተሰጠው አላህ ይባርክልህ አለው:: ከእውሩም ዘንድ በመምጣት: ይበልጥ የምትወደው ነገር ምንድን ነው?ሲል ጠየቀው::አላህ የዓይኔን ብርሃን መልሶልን ሰዎች መመልክት መቻል በማለት መለሰለት::አበሰው::አላህ የዓይኑን ብርሃን መለሰለት::ከገንዘብ የትኛውን ነው ይበልጥ የምትወደው? ሲልም ጠየቀው:: ፍየል አለ:: ወላድ የሆነች ፍየል ተሰጠው:: ሁሉም ተራብቡ ተበራከቱ:: አንደኛው አንድ ሸለቆ ግመል ሌላኛው አንድ ሸለቆ ከብት ሦሰተኛው ደግሞ የአንድ ሸለቆ ፍየል ባለሀብቶች ሆኑ::በሌላ ወቅት መላኢካ ድሮ በነበረው መልክና አኳኋን ሆኖ ለምፃም ወደነበረው ሰው መጣና: ችግር የደረሰብኝ መንገደኛ ነኝ::አላህና አንተ ከምትለግሱኝ ችሮታ በሰተቀር ጉዞየን ለመቀጠል የሚሰችለኝ ሰንቅ የለኝም:: ለመዳረሻየ የሚሆነኝ ሰንቅ ታቀብለኝ ዘንድ መልካም መልክ መልካም ቆዳና ይህን ሁሉ ግመል በለገሰህ አምላክ ሰም እማፀንሃለሁ አለው::አያሌ ጉዳዮች አሉብኝ ልረዳህ አልችልም አለው:: የማውቅህ ይመሰለኛል:: ሰዎች የሚፀየፉህ ለምፃምና ድሃ አልነበርክም?አላህ ጥሩ መልክና ቆዳ እንዲሁም ሀብት ለገሰህ አለው::”ከአያት ቅድመ አያቶቼ የወረሰኩት ነው”አለ::ሐሰት ከተናገርክ አላህ ድሮ ወደ ነበርክበት ሁኔታ ይመልሰህ አለው::መላጣ ወደነበረው ሰው በጥንቱ መልክና አኳኋን ሆኖ በመምጣትም ለዚያኛው ያለውን አለው::ይህኛውም ያኛው የሰጠውን ዓይነት ምላሸ መለሰለት::ሐሰት ከተናገርክ ድሮ ወደ ነበርክበት ሁኔታ አላህ ይመልሰህ አለው:: በጥንት መልክና አኳኋን ሆኖ እውር ከነበረው ሰው ዘንድ መጣና በጉዞ ላይ ሰንቅ የተቋረጠብኝና ችግር የደረሰብኝ መንገደኛ ነኝ::ከአንተና ከአላህ ከማገኝው ችሮታ ውጭ ለመዳረሻየ የሚሆን ሰንቅ የለኝም:: ለመዳረሻየ የሚሆነኝ አንዲት ፍየል ትሰጠኝ ዘንድ የዓይንህን ብርሃን በመለሰልህ አምላክ ሰም እማፀንሃለሁ? አለው::”እውር ነበርኩ አላህ ዓይኔን መለሰልኝ”::ያሻህን ውስድ:: በአላህ ይሁንብኝ! ልዑልና ሀያል ለሆነው አላህ ሰል ዛሬ የምትወሰደውን ነገር መልሰ ብዬ አላሰችግርህም አለው ገንዘብህን ያዝ እናንተን ለመፈተን ነው የመጣሁት::አላህ በአንት ረክቶ በሁለቱ ወዳጆቸህ ተቆጥቷል አለ:: (ቡኻሪና ሙሰሊም)

73) “ባለህበት ቦታ ሁሉ አላህን ፍራ (በትክክል ተገዛው)።ክፉ ሰርተህ ከሆነ ወዲያውኑ መልካም ስራ አስከትልበት፤
ያብሰዋልና። በመልካም ስነምግባር ከሰዎች ጋር ኑር።” የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) /ትርሚዚ የዘገቡት

74) አነስ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

እያንዳንዱ መልካም ተግባር ሰደቃ ነው።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) (ቡኻሪና ሙስሊም)

75) ረሱል (ሰ.ወ.ዐ) ሲናገሩ "የመልካም ጏደኛ ምሳሌ ከሽቶ ነጋዴ ጋር ሲገናኙ ካለዎት ገዝተው ከሌለዎት ከሽቶው መልካም ጠረን እንደሚያገኙ ያህል ነው::" ሙተፈቁን አለይሂ 

76)ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ከሴቶቻችሁ በላጯ ቤቷ ውስጥ ሽቶ የምትቀባ: ጥሩ ምግብ የምታዘጋጅ: አላግባብ ወጪ የማታወጣ ናት

77)  የአደም ልጀ ሆይ፡-ምድርን የሚያክል ወንጀል ብትሰራም በኔ ላይ ምንንም አካል ሳታጋራ ከተገናኘኸኝ ምድርን የሚያህል ምህረት ይዤ እጠብቅሃለሁ፡፡ ቲርሙዚ የአደም ልጀ ሆይ፡-ምድርን የሚያክል ወንጀል ብትሰራም በኔ ላይ ምንንም አካል ሳታጋራ ከተገናኘኸኝ ምድርን የሚያህል ምህረት ይዤ እጠብቅሃለሁ፡፡ ቲርሙዚ
78  አቡ ሁረይራ /ረ.ዐ/ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ /ሰ.ዐ.ወ/ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ‹‹አላህ፡ ‹‹ዱንያ ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል ወዳጁን ወስጄበት ከኔ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ /ትዕግስት ላደረገ/ ሙእሚን ባሪያዬ የምሰጠው ሽልማት ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡›› ይላል፡፡›› /ቡኻሪ እንደዘገቡት/ 
 79) አቡ ሁረይራ /ረ.ዐ/ እንዳስተላለፉት ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ እንዲህ ብለዋል ‹‹አንድን ሙስሊም አንድም ችግር ወይም በሽታ ሀሳብ ወይም ቁጭት የሚያውክ ነገር ወይም ጭንቀት አያገኘውም በምትወጋው እሾህ እንኳ አላህ በርሷ /ሰበብ/ ወንጀሎቹን ያበሰለት ቢሆን እንጂ!››/ቡኻሪ እንደዘገቡት / 

79. አነሰ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፍት የአላህ መልክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል
** ሪዝቁ እንዲሰፋለት እድሜው እንዲረዝምለት የከጀለ ዝምድናውን ይቀጥል**
(ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሱ የምንማራቸው ቁም ነገሮች
• ዝምድናን የመቀጠል ትሩፋት የዕድሜን ርዝመት የ "ሪዝቅ"ን ስፋት
ጤንነትን ከሞት በኋላ በበጐ መወሳትን መልካም ዝርያንና ለአላህ ትዕዛዝ ማደርን
ጊዜን በከንቱ ያለማባከን ፀጋ እርጋታንና ከፍተኛ ደስታን ያጐናጽፋል