የሴቶች መብት

  ከነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) መላክ በፊት የሴቶች መብት እና በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የነበራት ስፍራ በጣም የወረደ እና ይልቁንስ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብቶች እንኳን የማይሰጣት ምስኪን ፍጥረት ነበረች። በተለይም በአረቡ አለም። ሴት በመሆኗ ብቻ የመኖር መብት የተነፈገችበት ጊዜ ነበር። አንድ አባት ሴት ልጅ ስትወለድ ሀፍረትና ውርደት ነበር የሚሰማው፤ እናም ከዚህ ውርደት ጋር መኖር እንደሌለበት በማሰብ የተወለደችለትን ልጅ አይኗ እያየ ከነሕይወቷ ከሚረማመድበት ምድር ስር ይከታታል።

 በሌላ መልኩም ሴት ልጅን ሕይወት እንዳለው ፍጥረት ሳይሆን እንደ ዕቃ ነበር የሚመለከቷት፤ በጨዋታቸው ላይ እንደ ገንዘብ ሴት ልጅን ነበር አስይዘው ቁማር የሚጫወቱት። ከዚህ በበለጠ ደግሞ የሚገርመው ሴት ልጅ ሕይወት አላት ወይንስ የላትም የሚል ክርክር እና ውይይት የሚደረግባት ፍጥረት ሆና ቆይታ ነበር። ብቻ ብዙ ብዙ …

የነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) መላካቸው ግን እነዚህን ታሪኮች በሙሉ ቀያሪ ሆነ፤ የሴቶች ህይወት እንደገና አበበ። ሴት ልጅ እንደ ገንዘብ የምትወረስ ሳይሆን ወራሽነቷ ተረጋገጠ፣ ነገሩ ሴት ህይወት የላትም ሳይሆን የህብረተሰቡ ግማሽ አካል እንዲያውም ከዚያ በላይ መሆኗ ተረጋገጠ።

       ነገር ግን ይህን እና ሌሎችን መብቶች በማስተባበል የእስልምናን እውነታ ባለማወቅም ሆነ እያወቁ እስልምና ሴት ልጅን እንደሚበድል በተለያዩ ሚዲያዎችና የሀይማኖት ተከታዮች ይለፈፋል። እስቲ እስልምና ወይንስ ክርስትና የሴትን ልጅ መብት የሚያረጋግጠው …

የሴቶች መብት እና ክብር በመፅሐፍ ቅዱስ(በጥቂቱ)

  1. ወደ ጢሞቲዎስ 2፡12 -14   ሴት ልጅ ወንድን ማስተማርም ሆነ በወንድ ላይ ምንም ስልጣን ሊኖራት አይችልም ይህ የሚሆነውም በመጀመሪያ የተፈጠረው አዳም በመሆኑ ነው።
  2. ወደ ቆሮንጦስ 11፡ 5 – 10 ሴት ልጅ ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም፤ ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም።
  3. ኦሪት ዘዳግም 22፡28 ለሌላ የታጨችን ልጃገረድ ድንግልና የወሰደ ለአባቷ ሀምሳ ጥሬ ብር ዋጋ ይከፍላል እሷም ያለ ፍላጎቷ ሚስት ትሆናለች በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መፍታት አይችልም
  4. መፅሐፈ መሳፍንት 21፡20 ሴት ልጅን መጥለፍ እንደሚፈቀድ ይናገራል
  5. ኦሪት ዘሌዋዊያን 12፡2-8  – ሴት ልጅ ወንድ ልጅ ከወለደች ለ 7 ቀን ትረክሳለች

                            – ሴት ልጅ ሴት ብትወልድ ለ 17 ቀን ትረክሳለች

     በመርከሷም ምክኒያት የሚቃጠል መስዋዕት ሆኖ የሚቀርብ አንድ ጠቦትና ለሀጢያት ስርየት መስዋዕት የሚሆን ዕርግብ ወይንም ዋኖስ ለእግዚአብሔር ቤት ካህን መስጠት አለባት

    ከነዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በግልፅ የምንረዳው መፅሐፍ ቅዱስ (ክርስትና ለሴት ልጅ መብት የቆመ የሴት ተከራካሪ ሳይሆን ተፈጥሮአዊ መብቶቿን እንኳን እንዳልሆነ ነው።)

 የሴቶች መብት እና ስፍራ በኢስላም

  በኢስላማዊው የቤተሰብ መዋቅር ውስጥ ሚስት የቤቷ ንግስት ነች። ነቢዩ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል «ሚስት በባሏ ቤት ጠባቂ ነች እናም በቤተሰቡ ባህሪና ጉዳዮች ላይ ተጠያቂ ነች» ቡኻሪ የዘገቡት

–       ሴት ልጅ ከቤት ውጪ በሚከናወኑ ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ነፃ ነች ቡኻሪ የዘገቡት

–       ሴት ልጅ ረጅም ጉዞ ለማድረግ ብትፈልግ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይደርስባት ከቅርብ ቤተሰቧ ጋር (አባት፣ ወንድም፣ ባለቤት፣ አጎት፣ ልጅ) መሄድ ግዴታነቱን ኢስላም ደንግጓል።

–       ሴት ልጅ ያለምንም በቂ ምክኒያት ከቤት መውጣቷን ኢስላም አያበረታታም

–       ሴት ልጅ የትዳር አጋሯን የመምረጥ መብት አላት

–       ነቢዩ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል «አንዲት ሴት(አግብታ የምታውቅ) ከቤተሰቧ ይልቅ የራሷን እጣ የመወሰን መብት አላት አግብታ የማታውቅን ሴት ያለ ፍቃድ አታኑሯት»

–       ባሎቻቸው የሞቱባቸው የተፈቱ ሴቶች እና ጋብቻቸው በህግ ውድቅ የተደረገ ሴቶች አዲስ ትዳር የመመስረት ሙሉ በሙሉ መብት አላቸው።

«ለእነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በእነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡» ሱረቱ አል በቀራህ 228

–       ሴት ልጅ የመውረስ መብት አላት

 «ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት (ንብረት) ፋንታ (ድርሻ) አላቸው፡፡ ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት ከእርሱ ካነሰው ወይም ከበዛው ፋንታ አላቸው፡፡ የተወሰነ ድርሻ (ተደርጓል)፡፡» ሱረቱ አን ኒሳእ 7

–       ሴት ልጅ በሰብአዊነቷ ከወንድ እኩል ነች፤ ወንድም ሆነ ሴት ምንዳቸውን የሚያገኙት በሰሩት ስራ ልክ ነው።

«አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ፡፡ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፡፡   ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ አላህንም ከችሮታው ለምኑት፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡»   ሱረቱ አን ኒሳእ 32

 «ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡» ሱረቱ አል-አሕዛብ 35

ሴት ልጅ ታላቅ ስጦታ ናት

  1. «አካለ መጠን ደርሰው ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ ሁለት ሴት ልጆችን ያሳደገ የፍርዱ ቀን ከኔ ጋር እኩል ይቆማል» ብለዋል ሁለት ጣቶቻቸውን አጠጋግተው በማሳየት
  2. ሴት ልጆች ብቻ ያሉት ሰው እርሱም በትክክል ካሳደጋቸው ከጀሃነም እሳት ሽፋን ይሆኑለታል።
  3. ከመልካም ሚስት የበለጠ ፀጋ በዚህ አለም አይገኝም (ኢብን ማጃህ)
  4. አንድ ሰው ወደ ነቢዩ መጥቶ እንዲህ በማለት ጠየቀ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይበልጥ እንክብካቤ ላደርግለት የሚገባኝ ሰው ማን ነው?» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «አባትህ» አሉት። ወደ እናታችን በሶስት እጥፍ ስንቀርብ ወደ አባታችንአንድ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው። ይህም እናት የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ድርሻ ሲኖራት አባት የሰርተፊኬት ድርሻ ያገኛል ማለት ነው።

      የሴቶችን መብትና ክብር በእስልምና በዚህች ፅሁፍ የምናጠቃልለው አይደለም። ከባህር የማንኪያ ያህል ነው። ከዚህ ጋር መረዳት ያለብን ነገር ከማንም  እና ከምንም የበለጠ ለሴት ልጅ ክብርና መብት ተቆርቋሪ ከእስልምና ውጪ አልነበረም፤ የለም፤ አይኖርምም። በአለማዊ ጥቅማጥቅሞች እና በምዕራባዊያን propaganda በሚዲያን መሰረተ ቢስ አስተምህሮቶች ይህን የማንነት መገለጫ፤ የሕይወቷ መሰረት ፤ የስኬታማነቷ መንገድ የሆነውን ሃይማኖት ልትለቅ አይገባም!!!!!!!!!!!!!!!

ሰባቱ የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች (ሸርጦች)

1.ዕውቀት፡- ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት እና ቃሉ ዉድቅ የሚያደርጋቸዉንና እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡

وَلَا يَمْلِكُ الَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنْ شَهِدَ بِالْحَقِّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

الزخرف: ٨٦

(እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም) አል-ዙኸሩፍ 86

2.እርግጠኛነት፡- በአላህ ብቸኛ አምላክነት ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን ነው፡፡አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنْفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ

الحجرات: ١٥

({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም ያልተጠረጠሩት ናቸው) አል-ሑጁራት 15

የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡ ሑረይራ (ረዲየ አላሁ አንሁ) እንዲህ ብለውታል፡- ‹‹ ከዚህ አጥር በስተጀርባ የአላህን ብቸኛ አምላክነት ከልቡ በእርግጠኝነት የሚመሰክር ሰው ብታገኝ በጀነት አበስረው፡፡›› ሙስሊም ዘግበዉታል

3.መቀበል፡- የላኢላሀ ኢለላህን መልእክት (አላህን በብቸኝነት ማምለክን) ከልብ መቀበልና ለሌላ አካል የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው ነው፡፡ ይህንን ያልተቀበለ ግን አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸው እንዲህ በማለት ከገለፃቸው ሙሽሪኮች መደዳ ይሰለፋል፡፡

إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ

الصافات: ٣٥ – ٣٦

(እነርሱ፤ ‹ከአላህ ሌላ አምልኮት የሚገባው ሆኖ የሚመለክ አምላክ የለም› በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፡፡ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን ይሉም ነበር፡፡) አልሷፋት 35-36

4.መታዘዝ፡- ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል ለሚያመላክታቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَمَنْ يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَى وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

لقمان: ٢٢

(እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ) ወደ አላህ የሚሰጥ ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ…)

ሉቅማን 22

5. እውነተኝነት፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ እውነተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ ‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርም ይለዋል ›› ቡኻሪ ዘግበዉታል

6. መውደድ፡- ይህ ማለት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል ፡-

(وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَتَّخِذُ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَنْدَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِلَّهِ

البقرة: ١٦٥

(ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው) አል በቀራህ 165

7. ማጥራት፡- ይህም ማለት የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፡፡ እንዲሁም በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ ጥቅማጥቅሞችን ከመከጀል፣ ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ መጥራት አለበት፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ በማግኘት ዕድለኛ የሚሆነው ላ ኢላሀ ኢለላህን ከልቡ ያለ ሰው ነው፡፡›› ቡኻሪ ዘግበዉታል፡፡

ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ኢስላም ማለት የአላህ (ሱ.ወ) አንድነትን በማወቅና በማመን ለርሱ እጅ መስጠት፣ ለፍላጎቱና ትዕዛዛቱ ማደር፣ ተግባራዊ ለማድረግም በታዛዥነት መንፈስ መንቀሳቀስ፣ ከሽርክ (በአምልኮ ሌላን አካል ከርሱ ጋር ማጋራት) መጽዳት ነው። ይህም አላህ (ሱ.ወ) ያዘዛቸውን ነገሮች በመፈጸምና የከለከላቸውን ደግሞ በመራቅ ይረጋገጣል።

ኢስላም ከላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ብቸኛና እውነተኛ ሐይማኖት ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ [٣:١٩]

“አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው።” (አሊ-ዒምራን 3፤91)

አላህ (ሱ.ወ) ለመልክተኞቹና ነብያቶቹ በየዘመኑ ያወረዳቸው ህግጋቶች የተለያዩ ቢሆኑም ለሁለም ነብያትና ህዝቦች የወረዱት ህግጋቶች የአላህን አንድነት በማስተማር፣ ለሰው ልጆች ጠቃሚ ነገሮችን በማረጋገጥና ወደ መልካም ሥነ-ምግባር ጥሪ በማድረግ ያለቸው አስተምህሮት ተመሳሳይ ነው። እንደየ ዘመኑ ሁኔታና ለሰዎች ኑሮ አስፈላጊነት አኳያ አንዳንድ ህጎች ላይ ልዩነቶች ያሉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በየዘመኑ የወረዱት የአላህ (ሱ.ወ) ህግጋቶች ያላቸውም ስፋትና ጥበት የተለያየ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا [٥:٤٨]

“ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን።” (አል-ማኢዳ 5፤48)

ከሰማይ የወረዱት መለኮታዊ ህግጋቶች በብዙ ጉዳዮ ላይ ተመሳሳይነት ይንጸባረቅባቸዋል፤ ከነዚህም ውስጥ፡

  1. 1.መነሻ (ምንጭ)

የመለኮታዊ ህግጋቶች ምንጭ ከብቸኛውና አንዱ አምላክ አላህ.(ሱ.ወ) ስለሆነ ደረጃው ከፍ ያለ ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ [٤:١٦٣]

“እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን።” (አን-ኒሳእ 4፤163)

  1. 2.አላማ

መለኮታዊ ህጎች ከአላማዎች መካከል፡-

  • ሰዎችን ለጌታቸው ተገዥዎች እንዲሆኑ ማድረግ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ [٢١:٢٥]

“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።” (አል-አንቢያእ 21፤25)

በሌላ የቁርኣን አንቀጽም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ[١٦:٣٦]  

“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ‘አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ’ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል። ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ። ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ። በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ።” (አን-ነህል 16፤36)

  • ሰዎች ጌታቸውን እሱ በደነገገው ህግጋትና ባዘዘው መሰረት በፍቅርና በፍቃደኝነት መገዛት። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَن يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ [٢٤:٥١]

“የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ሰማን፤ ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው። እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።” (አን-ኑር 24፤51)

  1. 3.አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳቦች

መለኮታዊ ህጎች ጠቅላላ በሆኑ ጽንሰ ሐሳቦች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፤ ለምሳሌ ሁለም ሰው የስራውን እንደሚያገኝ፤ ጥሩ የሰራ ጥሩ ምንዳ እንደሚከፈለውና መጥፎ የሰራ ደግሞ ቅጣት እንደሚገባው፤ አንድ ሰው በሌላ ሰው ወንጀል እነደማይጠየቅና ከራሱ ሥራ ውጭም እንደማያገኝ ሁሉም መለኮታዊ ህጎች ይስማማሉ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ﴿٣٦﴾ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ﴿٣٧﴾ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ﴿٣٨﴾ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ﴿٣٩﴾ وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ﴿٤٠﴾ ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ﴿٤١﴾

“ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል።” (አን-ነጅም 53፤36-41)

ያለፉት መለኮታዊ ህጎችና መመሪያዎች ሁሉ ለአላህ. (ሱ.ወ) መታዘዝንና ከሰው ልጅ በመረጣቸው መልክተኞቹ አንደበት በደነገገው ህግ መሰረትም እርሱን ብቻ ማምለክን ያስተምራሉ።

የመጀመሪያው መልክተኛ ነቢ ኑህ (ዐ.ሰ) እንዲህ ይላሉ፡-

وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ [١٠:٧٢]

“ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።” (አን-ነምል 10፤91)

የነብያቶች አባት በመባል የሚታወቁት ነብዩላህ ኢብራሂምና ልጃቸው ኢስማዒልም እንድህ ይላሉ፡-

رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ [٢:١٢٨]

“ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን። ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ)። ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን)። በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና።” (አል-በቀራ 2፤128)

ነቢዩላህ ኢብራሂምና ነቢዩላህ የዕቁብም (ዐማ.ሰ) ዝርዮቻቸው ትክክለኛውን የአላህ ዲን ኢስላምን ብቻ ይዘው እንዲኖሩና እንዲሞቱ አደራ ሲሰጡ እንድህ ብለዋል

وَوَصَّىٰ بِهَا إِبْرَاهِيمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَا بَنِيَّ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ لَكُمُ الدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ [٢:١٣٢]

“በርሷም (በሕግጋቲቱ) ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ። ያዕቁብም (እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ)። ‘ልጆቼ ሆይ! አላህ ለናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ’ (አላቸው)።” (አል-በቀራ 2፤132)

ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ይህንኑ ከአላህ ሲለምኑ እንዲህ ይላሉ፡-

رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ [١٢:١٠١]

“ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ። ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ። የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ። ሙስሊም ሆኘ ግደለኝ። በመልካሞቹም አስጠጋኝ (አለ)።” (ዩሱፍ 12፤101)

ነቢ ሙሳ (ዐ.ሰ) ትክክለኛ አማኝ ማለት ለአላህ (ሱ.ወ) ያደረ ሙስሊም መሆኑን ለህዝባቸው ሲያስተምሩ እንዲህ ይላሉ

وَقَالَ مُوسَىٰ يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ [١٠:٨٤]

“ሙሳም አለ፡- ‘ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ። ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)’።” (ዩኑስ 10፤84)

ይህን ጉዳይ የሚያስረዱ ሌሎች የቁርኣን አንቀጾች በብዛት ይገኛሉ።

የኢስላም ልዩ ትርጓሜ

እንደሚታወቀው ለሰው ልጆች አስፈላጊና ጠቃሚ ነገሮች ከግዜና ሁኔታዎች መለያየት ጋር ተያይዞ ሊለያዩ ይችላሉ፤ ስለዚህም ጥበበኛ የሆነው ጌታ አላሁ (ሱ.ወ) ቀድሞ በእውቀቱ እንዳሳለፈው ለሰው ልጆች በየጊዜው ጠቃሚና አስፈላጊ የሚሆነውን ነገር ይደነግጋል፤ ስለዚህም ነው ሻሪ ከተሻሪ በአብዛኛው በላጭና የተሻለ ሆኖ የምናገኘው። ምክኒያቱም ከጥሩ ነገር ወደ በላጭ ነገር መሸጋገር አላህ (ሱ.ወ) በፍጡራኑ ላይ ያደረገው ተፈጥሯዊ ህግ ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) ባሮቹን ምንግዜም ቀስ በቀስ ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከጥሩ ነገር ወደ በላጭና ሙሉ ወደ ሆነ ነገር ይወስዳቸዋል።

ኢስላማዊ ሸሪዓ (ህግ) አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች መመሪያ ያወረደው የመጨረሻና የማይሻር መለኮታዊ ህግ ነው፣ ስለዚህ ሁሉንም የህይዎት ዘርፎች የሚዳስስና ሰፊ ይዘት ያለው ሆኖ እናገኘዋለን። የሸሪዓ ህግ ውስጥ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ድንጋጌዎች ናቸው ያሉት፤ አቅመ ደካማዎች እንደ ችሎታቸው የሚሰሩበት የተግራራ ሥርዐት ያለ ሲሆን ጠንካሮችና ብረቱዎችም ባለቸው አቅም ተጠቅመው ሐላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችሉ ጠንከር ያሉ ትዕዛዛት ይገኛሉ። ይህም አላህ (ሱ.ወ) ለባሮቹ ያለውን ሰፊ እዝነት ያሳያል። አላህ (ሱ. ወ) እንዲህ ይላል

ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ [٤٥:١٨]

“ከዚያም ከነገሩ (ከሃይማኖት) በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ። ስለዚህ ተከተላት። የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል።” (አል-ጃሲያ ፤18)

አላህ (ሰ.ወ) ነብያችን ሙሃመድን (ሶ.ዐ.ወ) በመላክ መሰረታዊ ጽንሰ ሐሳቦቹንና ድንጋጌዎቹን ያብራራበትና ለሰው ልጆች ሁሉም እንዲያደርሱት ወደ እሱም ያዘዛቸው ዲነል-ኢስላም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ለባለቤቱም የሚጠቅም ብኛው ሐይማኖት እሱ መሆኑን አወጀ። ስለዚህ ኢስላም ከሱ በፊት የነበሩትን ሐይማኖቶች ሁሉ ሽሯል፤ በመሆኑም ኢስላምን የተከተለ ለፈጣሪው ያደረ (ሙሰሊም) ማለት እርሱ ነው፤ ከኢስላም ያፈነገጠ ደግሞ ለፈጣሪው አላደረም ወይም ሙስሊም አይደለም ማለት ነው።

ወደዚህ የአላህ ዲን ኢስላም መግቢያ በሩ “ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሃመድ ረሱሉሏህ” በማለት የአላህን ብቸኛ አምላክነትና የነብዩ ሙሃመድ የአላህ መልክተኝነት መመስከር፤ የዚህ የሰጠኸውን የምስክረነት ቃል ድንጋጌዎችና ቅድመ ግደታዎች ተግባራዊ ማድረግና እንደዚሁም ይህን የምስክረነት ቃልህን የሚጻረርን ነገርን ሁሉ መራቅ ናቸው።

ታለቁ ጌታ አላህ (ሱ. ወ) እንድህ ይላል

وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ [٣:٨٥]

“ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው።” (አሊ-ዒምራን 3፤85)

ነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ

والذي نفس محمد بيده لايسمع بي أحد من هذه الأمة، يهودي ولا نصراني ثم يموت ولم يؤمن بالذي أرسلت به إلا كان من أصحاب النار )رواه مسلم(

“በዚያ የሙሃመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ፤ ከዚች ኡማ ውስጥ ማንኛውም ሰው የሁዳም ይሁን ነሳራ (ክርስቲያን) የኔን መልክት ሰምቶ በዚያ እኔ በተላኩበት ነገር (ኢስላም) ሳያምን ከሞተ (እርሱ) ከሳት ባልደረባዎች ነው።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

በዚህም መሰረት ከነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) መላክ በኋላ ያሉ አይሁድም ይሁን ክርስቲያን ወደ ኢስላም ካልገቡ በቀደምት ነብያቶቻው ማመናቸው አይጠቅማቸውም ማለት ነው፤ ምክኒያቱም ነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) ይዘውት የመጡት ዲነል-ኢስላም ከሱ በፊት የነበሩትን ሐይማኖቶች የሚሽር ስለሆነ ነው።